#FastMereja I ዘማሪ ጉቱ ሽፈራው «ቁልቁሉ» የተሰኘውን 3ኛ የመዝሙር አልበሙን ሊያስመርቅ መሆኑን አስታወቀ። አልበሙን አስመልክቶ ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን፣ የዝግጅቱ አጠቃላይ ዝርዝሮች ለህዝብ ይፋ ተደርገዋል።
እንደ ጋዜጣዊ መግለጫው ማብራሪያ፣ ዘማሪ ጉቱ ሽፈራው ከዚህ ቀደም “ኦልቻ” የተሰኘ የመጀመሪያ የመዝሙር አልበም እና “ደጋ ጐሌ” የተሰኘ ሁለተኛ የመዝሙር አልበም ለህዝብ አድርሷል።
ባለፈው የሥራ ዘመኑ ከፌኖ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን እንዲሁም በጉለሌ ቤተል ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ታላላቅ የመዝሙር ድግሶችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ በእነዚያው መርሃ ግብሮች ላይ የ1970ዎቹን አርበኞችና አባቶች ዘማሪያን በመጋበዝ ተገቢውን እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።
አሁን ሶስተኛው “ቁልቁሉ” የመዝሙር አልበም የፊታችን እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ ኪዳን ካህናት ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን (አዲስ አበባ ገርጂ አጥቢያ) በድምቀት እንደሚመረቅ ተገልጿል።
ለታዳሚዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርም ከአራቱም አቅጣጫዎች ወደመርሃ ግብሩ ማዕከል የሚያደርስ የትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱ በመግለጫው ተመላክቷል።
አዘጋጆቹ እና ዘማሪው በመርሃ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት፣ የወንጌል አማኞች እና አጠቃላይ ምዕመናን በሰዓቱ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ኹነት




