banner

ለተከታታይ 4 ጊዜ እርግዝናዋ የተስጓጎለባት እናት፣ በ5ኛው እርግዝናዋ የአብራኳን ክፍያ ማቀፍ ቻለች።

#FastMereja I ነዋሪነቷን በጅማ ከተማ ያደረገችው ወይዘሮ ሰሚራ መሰለ የአብራኳን ክፍያ ለማቀፍ ሽታ በተጋጋሚ ጸንሳለች።

ዳሩ ግን እዳሰባችው ሳይሆን ቀርቶ በተከታታይ 4 ጊዜ ጸንሳ ባላዉቀችው የጤና እክል ምክንያት ጽንጽ ጠፍቶባታል።

ተስፋ ያልቆረጠች እናት በሆድዋ የተጸነሰው 5 ኛው እርግዝና በጅማ ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል ተደረገላት የእርግዝና ክትትልና አስፈላጊው ህክምና የጓጓችለትን ልጇን እድታቅፍ ረድቷታል።

እናት ለመሆን ጓጉታ በደጋጋሚ እርግዝናዋ የተስተጓጎለባት ሰሚራ የእርግዝና ክትትልና ምርመራ አለማድረጌ ለተደጋጋሚ ችግር ዳርጎኛል ትላለች።

ጥንካሬና ተስፋ ያለመቁረጥን የሰነቀችው 13 አመታትን በስደት ያሳለፈችው እናት፣ ለነበረው የጤና ችግር በጊዜ ተመርምሮ ምፍቴ ያለማበጀትና የእርግዝና ክትትል ያለማድረግ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘቧን በመግለጽ ከኔ ተማሩ ብላለች።

በመጨረሻም ባለቤቷ ከአቶ ረሻድ ከማል አስቅድመው ባላወቁት የሾተለይ የጤና እክል ምክንያት ጽንሱ እንዳይስተጓገል የጤና ባለሞያዎቹ ባደረጉላት ድጋፍ እና ህክምና አይኑን በአይኑ በማየቱ መደሰቱን ገልጿል።

በጅማ ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል የማህጽን እና ጽንስ ሀኪም እንዲሁም የፔቶ ማተራል ሜዲስን ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ደጀኔ አሰፋ እናቲቱ ለተዳጋጋሚ እርግዝና መስተጓጎል የዳረገው በተለምዶው ሾተላይ በህክምናው (Rh-isoimmunization) የእናትና የልጅ የደም አይነት (Rh factor) አለመጣጣም የጤና እክል መሆኑን ያስረዳሉ።

ይህን ችግር በመገንዘብ እደም አይነቷን በመለየት በሆዷ የለው ልጅ በደም ማነስ እንዳይጎዳ O- (O minus ) ደም በመስጠትና እናት አጋጥሟት ለነበረው የደም ግፊትን በማከም ጤናማ ልጅ እንድትገላገል መደረጉን ዶ/ር ደጀኔ ተናግረዋል።

ሴቶች እርግዝና ከመፈጠሩ በፊት የደም አይነታቸውን ማወቅ ፣የእርግዝና ክትትል ማድረግ ሾተላይን ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ህክምና እና ክትባት በመስጠት አስቀድሞ መከላከል እንደሚያስችል ዶ/ር ደጀኔ አስረድረዋል።

በወርቅአፈራው ያለው



Leave a Comment