banner

ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለመከላከል አከናወነች በተባለው ውጤታማ ሥራ ተሸለመች

ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለመከላከል በሰራችው ውጤታማ በተባለ ሥራ በተባበሩት መንግስታት ሥነ ሕዝብ ድርጅት እውቅና ማግኘቷን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ ። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በትናንትናው እለት በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ሽልማቱን መቀበላቸውን መገናኛ ብዙሀኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃን ጠቅሰው ዘግበዋል። ሚኒስትሯ እውቅናና ሽልማቱ መንግስት ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ የሚያጠናክር ነው ማለታቸውም ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ሥነ ህዝብ ድርጅት (UNFPA) የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስወገድ የተቋቋመውን ጥምረት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል ።

Leave a Comment