መጪውን አዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ‹‹ዘመን ተዋሕዶ ኤክስፖ›› በሚል መጠሪያ ‹‹ለጋራ እድገት በአብሮነት›› በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 12 አስከ 21/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 10 ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ ሐምሌ 6/2016 ዓ.ም በጁፒተር ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።
ይህ የተዋሕዶ ኤክስፖ ፕሮጀክት ከተለመደው የኤግዚቢሽን እና ባዛር አቀራረብ ለየት ባለ መልኩ በልዩ አውደ ምህረት ቅኝት እና ሁሉን አካታችን በሆነ መዋቅር እጅግ አነስተኛ በሆነ የመገቢያ ዋጋ በማቅረብ ከአልኮል መጠጥ እና ከሀይማኖታዊ ስርዓቱ ውጪ ከሆኑ ምርቶች ውጪ ያሉ የትኛውም የቤተ ክርስቲያን እና የማህበረሰብ መገልገያ ቁሳቁሶችን በማካተት የህብረተሰቡን አቅም ያማከሉ ምርት እና አገልገሎቶችን በማቅረብ በዘላቂነት በመስራት የህብረተሰቡ የኑሮ ገብአቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት የገበያ አማራጭ የማድረግ አላማ ያለው እንደሆነ አዘጋጆቹ ተናግሯል።

ዘመን ተዋሕዶ ኤክስፖ ላይ በቀን ከ5ሺህ ህዝብ በላይ እንደሚጎበኘው የሚጠበቅ ሲሆን ከ150 በላይ ነጋዴዎች እንደሚሳተፉም ተነግሯል። 10 ታላላቅ ጉባኤዎች በማታው መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ደቀርባል። በቂ የመኪና ማቆሚያ እና ልዩ የህጻናት ማቆያ እንደተዘጋጀ ተገልጿል።
ይህን የመጀመሪያ የዘመን ተዋሕድ ኤክስፖ ማርኮናል ኢንተርቴመንት እና ኤቨንት፣ ከሎዛ ኦርቶድክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ እና ከመንፈሳዊ ቲክቶከሮች ጋር በጋራ በመሆን እንደተዘጋጀ ተነግሯል። ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የመግቢያ ዋጋ 50 ብር እንደሆነ ተገልጿል።