banner

በዶናልድ ትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ማንነት ታወቀ

የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ቶማስ ማቲው ክሩክስ የተባለ የ20 ዓመት ወጣት መሆኑን አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው በጆሯቸው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ጥቃት ፈጻሚው ወደ ዶናልድ ትራምፕ ከመተኮሱ በፊት የሕዝብ መጨናነቅ በነበረት ቅስቀሳው ላይ ሌላ ሰው መግደሉም ተሰምቷል። ግለሰቡ ወዲያውኑ በደህንነት ሰዎች የተገደለ ሲሆን ሕግ አስከባሪዎች ይህ ክስተት እንዲፈጠር ያሳዩት ክፍተት ጥያቄ እያስነሳ ነው።

Leave a Comment