banner

የመ/ር ሥዩም ጉልላት ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጅ መ/ር ሥዩም ጉልላት ሥርዓተ ቀብር ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የመምህር ሥዩም ጉልላት ቤተሰቦችና ዘመዶች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በሥርዓተ ቀብሩ ጸሎተ ፍትሐት የተከናወነ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ትምሕርተ ወንጌል ተሰጥቷል። በትምሕርታቸውም አሽከርካሪዎችና እግረኞች በመንገድ አጠቃቀም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል። መ/ር ሥዩም ጉልላትበ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የነበሩ ሲሆን በ37 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ሕይታቸው ማለፉ ይታወሳል።

Via: EOTC TV

Leave a Comment