0

የኢትዮጲያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ-ክርስቲያን “በመልካም ወጣት” በሰባት አመት 180ሺ ወጣቶችን ማሰልጠን እንደተቻለ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ዛሬ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው መግለጫ ተገልጿል።
ቤተ ክርስቲያኗ በየአመቱ የምታካሂደው የመልካም ወጣት መርሃ ግብር ዘንድሮም “መልካም ወጣት ወደ ብርታት” በሚል መሪ ሃሳብ በዚህ አመትም 30ሺ ወጣቶችን በሐዋሳ ለማሰልጠን እንደተዘጋጁ ፓስተር ዮናታን ገልጿል።

በሐዋሳ ከተማ ከ1.2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ 70 በመቶ መድረሱን ፓስተር ዮናታን ተናግሯል፣ ቀሪው በሁለት አመት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብሏል።
በተጨማሪም በወላይታ ሶዶ የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን በ100ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ በ500 ሚሊዮን ብር ጥራቱን የጠበቀ በሱስ የተጠቁ ወጣቶች የማገገሚያ ተቋም የሚሆን እና ለመቶ ሺዎች ተደራሽ መሆን የሚችል የሆስፒታል ግንባታ እንደተጀመረ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።
በዘንድሮ መልካም ወጣት ምዝገባ ለአንድ ሰው 1,500 ብር መሆኑ ተገልጿል።