banner

ጥቁር አደይ ፊልም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ለዕይታ ሊቀርብ ነው!

#FastMereja
በአለም አቀፍ የፊልም መስፈርት የተሰራው የተባለው ጥቁር አደይ ፊልም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ከነሃሴ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ መታየት እንደሚጀምር ተገለፀ።

ጥቁር አደይ የፊልሙን የሃገር ዉስጥ የተመልካች ፍላጎት በመመልከት ለሃገር ዉስጥ ተመልካቾች በቴሌቲቪ በኩል መቅረቡ ተነግሯል። ለዚህ ፍላጎትም ቴሌቲቪ አስተማማኝ እና ተስማሚ ሆኖ ስላገኙት ፊልማቸዉን በቴሌቲቪ ለማሳየት መወሰናቸዉን የፊልሙ አዘጋጆች ገልጸዋል።

ፊልሙ ላይ ናታይ ጌታቸው፣ ካሳሁን ፍሰሃ ማንዴላ ፣ ነብዩ እንድሪስ እና ሌሎች ተዋንያን ተሳትፈውበታል ።

ዶቃ ፊልም ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ቴሌቲቪ ላይ በይፋ መታየት መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ጥቁር አደይ ፊልም ቴሌቲቪ ላይ ገብቷል።

ቴሌቲቪ ለገበያው አዲስ እና በአይነቱ የመጀመሪያ (streaming platform) (ቢሆንም በተመልካቾች ዘንድ መልካም አቀባበል እንዳለው የኢግልላይን (eagle-lion ) መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በእርሱፈቃድ ጌታቸው ገልጸዋል። ቴሌቲቪ የፊልም ኢንደስትሪውን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የገለጹት አቶ በእርሱ ፈቃድ እንደ ጥቁር አደይ ያሉ ፊልሞች ወደ ቴሌቲቪ መግባታቸው ትልቅ አስተዋጾ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ቴሌቲቪ ኤግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ከኢትዮቴሊኮም ጋር በአብሮነት ለገበያ ያቀረበው (strearning platform) ነው። ኤግልላይን በፋይናንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶቹ የሚታወቅ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሲሆን ዱቤአለ ፣ ካሽጎ (it is my dam)፣ ጌትሩምስ እና ጉዞጎ ለሕዝብ ይፋ ካደረጋቸው የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ዉስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





Leave a Comment