banner

ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ በተለያዩ የትምሀርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ከ800 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

#FastMereja
ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ በተለያዩ የትምሀርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ከ800 በላይ ተማሪዎች ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የትምሀርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በማስተርስ፣ በድግሪና በዲፕሎማ በአምባሳደር ሲኒማ አዳራሽ በድምቀት አስመርቋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ቴዎድሮስ አበበ ተቋማቸው በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዲፕሎማ፣ በዲግሪና በማስተርስ መርሐግብር በቀንና በማታ ትምህርት ተማሪዎችን ማስመረቁን የገልፀው በ2016 ዓ.ም. የማስተርስ መርሐ ግብር 109 ወንድና 82 ሴት በድምሩ 191ተማሪዎች እንዲሁም በዲግሪ መርሐግብር 311 ሴትና 279 ወንድ በድምሩ 590 ተማሪዎች በዲፕሎማ መርሐግብር 52 ሴትና 58 ወንድ በድምሩ 110 ተማሪዎችን ተቋሙ በዛሬው ዕለት ማስመረቁን ተናግረዋል።

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተቋሙ ተመራቂዎች ሴቶች መሆናቸውም በምረቃው ወቅት ተገልጿል።





Leave a Comment