#FastMereja
በ1996 ዓ.ም የተመሠረተው እና የወንዶችን ፀጉር በማስተካከል ሥራን በማዘመን የሚታወቀው ሪቾ ስማርት የወንዶች ፀጉር ቤት ለ32 ባለሙያዎችም የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በመጪው ዓመት 2017 ዓ.ም የወንዶች ፀጉር ስራ ማሠልጠኛ ተቋም እንደሚከፍት ዛሬ 18/12/2016 ዓ.ም ማፊ ሞል በሚገኘው ድርጅቱ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
የድርጅቱ ባለቤት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ራሄል ሙሉጌታ ለፋስት መረጃ እንደተናገሩት ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ 3 የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም ለዘውዲቱ ሆስፒታል፣ ለሚኒሊክ ሆስፒታልና ለጳውሎስ ሆስፒታል እንዲሁም ላቭ ኤንድ ኬር ለሚያገለግላቸው ማሳደጊያ ውስጥ ላሉ ህጻናት በየቀኑ ለአምስት መቶ ህፃናት ከሰኞ 20/12/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ ፀጉር የማስተካከል አግልግሉት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
ሪቾ ስማርት የውበት ማዕከል በደንበኞች ዘንድ የተመሠገነ ድርጅት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ ሲጠቀሙ ከነበሩ ደንበኞች መረዳት ተችሏል ከነዚህም ደንበኞች መሀከል በሚዲያ የምናውቃቸው አቶ እዝራ እጅጉ አንዱ ናቸው ባለፉት 20 ዓመታት ሲጠቀሙ እንደነበር ገልፀው አገልግሎቱ ዘመናዊ እና ምቹ እንደነበር ገልፀዋል።





1 comment
ለኛ ለመላጣዎቹ ብሩን ይስጡን 😎