banner

ወጣቶች የሚሳተፉበት አራተኛው ዓመታዊ የአመራር ኮንፈረንስ እና ውድድር ነሃሴ 24 እንደሚጀምር ተገለፀ

አራተኛው ዓመታዊ የአመራር ኮንፈረንስ እና ውድድር (LCC) “የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እና የኢኮኖሚ እድገት” በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አምባሳደሮች ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በተገኙበት ከነሀሴ 24 እስከ ነሃሴ 25/12/2016 ዓ.ም ድረስ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ በዛሬው ዕለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

የዘንድሮው ዓመታዊ የአመራር ኮንፈረንስ እና ውድድር (LCC) በአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና በኢኮኖሚ እድገት መካከል ያለውን ውስብስብ እና ትስስር የሆኑ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ውይይቶች፣ ሀሳቦችን የሚቀሰቅሱ ፓናሎች እና አነቃቂ ቁልፍ ንግግሮች፣ እንዲሁም ተሳታፊዎች ማህበረሰባችን እያጋጠሟቸው ሰላሉ ችግሮች እና ለሚያጋጥሟቸው ውስብስብ ተግዳሮቶች አዳዲስ መፍትሄዎችን እንዲያመጡ የሚፈጠርበት መድረክ ይሆናል ተብሏል።

ዓመታዊ የአመራር ኮንፈረንስ እና ውድድር (LCC) በተባበሩት መንግስታት የወጣቶች የውይይት መድረክ መሰረት የሚዘጋጅ በኢትዮጵያ ትልቁ የዲፕሎማቲክ ሲሙሌሽን ዝግጅት በመሆን ላለፉት ሶሰት ተከታታይ አመታት ለወጣት መሪዎች፣ ተማሪዎች እና ታዳጊ ዲፕሎማቶች በዲፕሎማሲ፣ በአመራር እና በውጤታማ ሰላማዊ ውይይት እንዲሁም አለማቀፋዊ የመፍትሄ ሀሳቦችን ማርቀቅ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ወሳኝ ሚና ተጫቷል። ይህ ክስተት ለአለምአቀፍ ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ልዩ እድል ይሰጣል እናም ተሳታፊዎች የዓለምን የወደፊት ሁኔታ በሚወስኑ አስፈላጊ ውይይቶች ላይ እንዲሳተፉ ያበረታታል ተብሏል።

ሴፍ ላይት መሰረቱ “የማህበረሰቡን አስተሳሰብ መቀየር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነዉ” በሚል መሪ ቃል ላይ የተመሮከዘ ሲሆን ይህም ሰዎች ሀሳባቸውን ወደ ተግባራዊ መፍትሄዎች እንዲቀይሩ ፤ የግል ህይወታቸውን እንዲሁም ሀገራቸውን በመልካም ግንባታ እንዲያንፁ እድሎችን ለማበረከት እና ችግሮችን የመፍታት ዕምቅ ችሎታዎችን ለማነሳሳት እና ለማብቃት ይሰራል። ዋና ተልዕኮው ወጣት መሪዎችን ለማህበረሰቡ ችግር ተጨባጭ የሆነ ለውጥን አንዲያመጣ ማድረግ ሲሆን በአመራር እና ዲፐሎማሲ፣ ስራ ፈጣሪነት፣ ሰላም ግንባታ፣ እንዲሁም የዲጂታል ልህቀት ዋና የትኩረቶቻን ማዕከል ናቸው ፡፡

ላይት ኢኒሼቲቭ በ2018 በአምባሳደር ስለሺ “ሳልስ” ኡመር የተመሰረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ ኩባንያ ሲሆን እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2018 በመመዝገቢያ ቁጥር 4906 በአዋጅ ቁጥር 1113/2006 እና ማህበራዊ ኢንተርፕራይዝ ድርጅት በንግድ አዋጅ ቁጥር 980/2016 የተመዘገበ ድርጅት ነው።





Leave a Comment