0
#FastMereja
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባልተፈቀደ ቦታ ሽንት የሸኑ 22 ግለሰቦች መቅጣቱ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረደ 11 ባልተፋቀደ ቦታ ሽንታቸውን ሸንተው አካባቢ ያቆሸሹ 22 ግለሰቦች በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት 22 ሰዎች እያንዳንዳቸው 2000 ሺህ ብር አጠቃላይ 44,000 ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማደረጉ ገልጿል ።
በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የህዝብና የመንግስት የሆነ መሬት በህገወጥ መንገድ በመውረር ታጥሮ የነበረ 5 ቦታዎች በአጠቃላይ 2,200 ካሬ ሜትር መሬት በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እርምጃ መወሰዱ ባለስልጣኑ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በህገ ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
