banner

ራይድ ትራንስፖርት ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ ፡፡

#FastMereja
ራይድ ትራንስፖርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለሚያቀርበው የትራንስፖርት አገልግሎት የአሽከርካሪዎችን ፣ ባለንብረቶችን እንዲሁም የውድ ደንበኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችለውን ስምምነት ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ጋር ተፈራርሟል :: ስምምነቱ የተፈረመው ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን በስምምነት ስነ- ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በከተማዋ የሚስተዋለው የትራንስፖርት እንቀስቃሴ ሰላማዊ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲቀጥል በትኩረት ይሰራል ብለዋል::

ራይድ የትራንስፖርት አገልግሎትም የነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነንት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ የመግባቢያ ስምምነት የከተማችን ነዋሪዎች የራይድ ትራንስፖርትን ሲጠቀሙ የፀጥታ ስጋት እንዳያጋጥማቸው አሰራሩን ከፖሊስ መምሪያው ጋር በዘመናዊ እና አስተማማኝ አሰራር ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም የአሸከርካሪዎችና የተሸካርካሪ ባለንብረቶች ለሚያጋጥማቸው ማንኛውም የደህንነት ስጋቶችና ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ::

ድርጅታችን የአሽከርካሪዎችም ሆነ የውድ ደንበኞቹን ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት የስምምንቱን አስፈላጊነት ተረድቶ ስምምነቱን የተፈራርመ ሲሆን በዚህም ቀደም ሲል የነበረውን አሰራር የበለጠ በማዘመን እና አገልግሎቶቹን በቴክኖሎጂ በማስተሳስር ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችለውን ወሳኝ ምዕራፍ ጀምሯል :: የነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነት የጋራ አጀንዳ በማድረግ ለሚሰሩ ማንኛውም አይነት ስራዎችን ከፖሊስ መምሪያው ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመግባቢያ ስምምምነቱ የራይድ ትራንስፖርት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞችም ሆኑ አሽከርካሪዎች በሰላም ወጥተው መግባት ይችሉ ዘንድ እንዲሁም የወንጀል መከላከል ስራዎቸን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመከወን ከፖሊስ መምሪያው ጋር በቅርበት በመቀናጀት ይሰራል :: አዳዲስ እና ዘመናዊ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚሰጠውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስፋት የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ በስምምነቱ ላይ ተመልክቷል ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ በመዋናነት ሦስት መሠረታዊ ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያው የትኩረት አቅጣጫ ወንጀልን ቀድሞ መከላከል ላይ በሚሰሩ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ የደንበኞችን፣ የአሽከርካሪዎችን እና የባለንብረቶችን ደህንነት ለማስጠበቅ ዘመናዊና አስተማማኝ የቴክኖሎጂ ትስስር ስራዎችን በማጠናከርና ተግባራዊ ማድረግ የወንጀል መከላከል ስራዎችን ቅደሚያ ሰጥቶ ይሰራል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለሚፈጠሩ የደህንነት ስጋቶች እና ወንጀሎች የSOS ወይም የድንገተኛ ጥሪ ማሳወቂያ መልዕክቶችን በመተግበር ፣ ለወንጀል ድርጊቱ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረት በመስጠት ከፖሊስ መምሪያው ጋር በቅርበት እንደሚሰራ እና በሶስተኛው የትኩረት ነጥብም በድንገት ለወንጀል ድርጊት ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦችን በቅርበት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የሚያገግሙበትን አሰራር በማዘመን፣ እንዲሁም ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ ተገቢው ቅጣት እና እርምት እንዲሰጥ በመከታተል እና ፣ ውጤቱንም ዳር ማድረስ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡

ድርጅታችን ራይድ ትራንስፖርት በቀጣይም የቴክኖሎጂ አድማሱን በማስፋት የውድ ደንበኞቹን፣የአሽከርካሪዎችን እና የባለንብረቶችን ደህንነት የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ቁርጠኝነቱን ያረጋግጣል፡፡

RIDE በ Hybrid Designs PLC – በኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን በ LTM/3140 በብቸኝነት የመጠቀም መብት የተመዘገበ የንግድ ስም እና ዓርማ ሲሆን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ በማንኛውም መልኩ መጠቀም በህግ ያስጠይቃል!

2 comments

Nafyad August 28, 2024 - 4:43 pm

ከእናንተ ሽርጉድ ቴሌግራም ላይ የተከፈተ አንድ የራይድ ሹፌሮች ግሩፕ ብዙዎችን ከስርቆት ታድጓል።

Reply
Ermias Hailemariam August 28, 2024 - 5:20 pm

ጥሩ ተግባር ነው የሹፌሮችም የተሳፋሪዎችም ደንነት ይጠበቃል

Reply

Leave a Comment