0
#FastMereja
ይህ አሽከርካሪ መላኩ ይባላል የምስራቅ በለሳ የጎሀላ ወረዳ ልጅ ነው የልጆች አባት ነበር በዛሬው እለት 22/12/2016 በምዕራብ ጎንደር ዞን ከጭልጋ መተማ መንገድ ከሰራባ ወረድ ብሎ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች እርሱን በጥይት ደብድበው በመግደል ሌሎች 3 ሾፌሮችን አፍነው መውሰዳቸውን የሾፌሮች አንደበት ዘግቧል። እዚህ አካባቢ ከሳምንት በፊት 5 ሾፌር እና ረዳቶች 1 ነጋዴ መገደሉ የሚታወቅ ነው ::
ይህ አካባቢ በተደጋጋሚ ሾፌር የሚታፈንበት የሚገደልበት ቢሆንም ችግሩን በማየት ዘራፊወችን ለመያዝ ሆነ ቦታወችን ለይቶ በመጠበቅ ለመከላከል የሚደረግ ጥረት እንደሌለ አሽከርካሪዎች ይገልፃሉ ::


1 comment
የኢትዮጵያ መጨረሻ ያሳየናል 😭👏