banner

የጫኝ እና አዉራጅ ህግ እና ደንብ ከጸደቀ በኋላ ከዚህ ቀደም ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎች መፈታታቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ሪልስቴቶች እና የማኅበር ቤቶች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተደራጁ ጫኝ እና አውራጆች ነዋሪዎችን ለእንግልት እና ምሬት ሲዳርጉ መቆየታቸው ተደጋግሞ ሲነገር ይሰማል።

ይሄንን ችግር ለማስቀረትም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጡን በሕግ እና ሥርዓት ለመከታተል ህግና ደንብ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ለእያንዳንዱ ዕቃ የዋጋ ተመን የመጫኛ እና ማዉረጃ ዋጋ ጥናት በማድረግ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው አክለዉም በበጀት አመቱ 7ሺህ 268 ጫኝ እና አዉራጅ ወጣቶችን እንዲሁም 618 ማህበራትን በማሰልጠን መልሶ ማደራጀት እንደተቻለ ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም የተቀመጠዉን ህግ እና ደምብ ተላልፈው በተገኙ 115 ጫኝ እና አዉራጆች ላይ እስከ እስራት የደረሰ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።

በዚህ መሰረትም ህጉ ከወጣ በኋላ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎች በከፊል መቀነሳቸውን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ከባለቤቱ ፍላጎት ውጪ ማንኛውንም ዕቃ “እኛ ነን የምናወርደው” ማለት፣ ከፍ ያለ ዋጋ መጠየቅ እና መሰል ጉዳዮች አሁንም ድረስ የከተማዋ ነዋሪዎች ደጋግመው የሚያነሧቸው ችግሮች እንደሆኑ ይታወቃል።

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

2 comments

Tesfalem Arficho September 16, 2024 - 8:24 am

ጫኝና አውራጅ 🤝 ውንብድና + ስግጥና

Reply
Muha Love September 16, 2024 - 8:27 am

ኦሮሚያን ብታይ . .,

Reply

Leave a Comment