banner

በጃፓን በቀን ከ 100 ጊዜ በላይ ለሚስቱ ስልክ ሲደውል የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

የ38 አመቱ ጃፓናዊ በገዛ ሚስቱ ስልክ ላይ በቀን ከ100 ጊዜ በላይ ማንነቱን ሳያሳውቅ ሲደውል የቆየ ሲሆን ስልኩን ስታነሳም አንዳች ነገር ሳይናገር ዝምታን ይመርጥ እንደነበር ተደርሶበታል።

በሀምሌ ወር መጀመሪያ የ31 ዓመቷ ሴት በጃፓን ሃይጎ ግዛት፣ አማጋሳኪ በብስጭት ስልኩን እስክትዘጋ ድረስ ዝም ከሚለው ሰው እንግዳ የሆኑ የስልክ ጥሪዎችን መቀበል ጀመረች። ይህ ለሳምንታት ቀጠለ፣ ምክንያቱም ጥሪ ከማይታወቅ ስልክ ቁጥር የሚደወሉ በመሆናቸው ጥሪዎችን ማገድ አልቻለችም። በአብዛኛዎቹ ቀናት በደርዘን የሚቆጠሩ የስልክ ጥሪዎች ታገኛለች፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ፣ ስልክ ደዋዩ በቀን ከ100 ጊዜ በላይ ይደውላል። እንደ እድል ሆኖ፣ ስልኩ በሌሊት ወይም በባሏ ስልክ ላይ የቪዲዮ ጌሞችን ስትጫወት በጭራሽ አይደወልም።

ይህ ሚስጥራዊው ደዋይ ማን ሊሆን ይችላል የሚለውን ይበልጥ እንድታስበው ኡድርጓታል። የሐምሌ ወር አብቅቶ ወደ ነሐሴ ሲሻገር የስልክ ጥሪዎች እየጨመረ ይሄዳል። ተስፋ የቆረጠችው ወጣቷ ደዋዩን የምታጋልጥበትን መንገድ ማሰብ ትጀምራለች። የጥሪዎቹን ሰዓት ስትመለከት ባሏን የበለጠ ትጠራጠራለች። ምንም አይነት የስልክ ጥሪ የማይኖረው ምሽት ላይ አንድ አልጋ ላይ ሲተኙ እና በእርሱ ስልክ የቪዲዮ ጌም ስትጫወት አይደወልላትም። በመጨረሻም የ31 ዓመቷ ሴት ምስጢሩን ለመፍታት እንዲረዷት ለፖሊስ ታመለክታለች።

ባሏ ወንጀለኛ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳላትም ጠቁማለች። ምርመራ ከተካሄደ በኋላ የፖሊስ መኮንኖች የሴትየዋን ፍራቻ አረጋግጠዋል። ባለቤቷ በአማጋሳኪ የጃፓን ፀረ- ረብሻ ህግን በመጣስ ተይዟል።ባልየው ባደረገው አስገራሚ ጥሪ የገዛ ሚስቱን ከአንድ ወር በላይ ያስቸገረው ለምን እንደሆነ ሲጠየቅ፣ ሰውየው በቀላሉ “ሚስቴን አፈቅራታለሁ፣ ምንም ሳልናገር ስልክ እደውልላት” ነበር ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በጃፓን ውስጥ ያሉ ባለትዳሮች ተለያይተው መኖር የተለመደ ነው።በተለይም አንዳቸው በሥራቸው ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ሲደረግ አንዳንድ ጊዜ አንደኛው የትዳር ጓደኛ በቅናት ስሜት በስልክ መረበሽ እና መሰል ተግባራት ይፈፀማሉ። ሆኖም በአማጋሳኪ የሚገኙት ፖሊሶች እነዚህ ጥንዶች አብረው እየኖሩ የስልክ ጥቃት መፈፀሙን ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አረጋግጠዋል።

Via: ዳጉ ጆርናል

Leave a Comment