0
#FastMereja
አርቲስት ሜላት ነብዩ በ2017 አዲስ አመት ብሩህ ተስፋን በመሰነቅ የአዲስ አመት መልካም መአዛ ያለው ገጸ በረከት አድርጋ አሪቲ፤ መጣን፤ የሱ፤ የሷ የቴል እንዲሁም ንጉሳዊ በሚል ስያሜ እጅግ ውብና ማእዛቸው ያማሩ ሽቶዎችን ማምጣቷን ገለፀች።
ሜላት በሀገር ውስጥ እየተመረቱ ያሉትን ሽቶዎች አለም አቅፍ እውቅናን እንዲያገኙ አንዲሁም በአለም አቀፍ ገበያ ግንባር ቀደም ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ ዝግጅቷን ጨርሳ በመንቀሳቀስ ላይ እንደምትገኝ ተነግሯል።
በዛሬው እለትም ሉድ ቪክ ቪክቶርዮ የሜላት ሽቶ የክብር አምባሳደር በመሆን የሀገሩን ምርት የሆነውን መልካም መአዛ ያለውን ሜላት ሽቶ ለሀገራችን ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ በክብር አምባሳደር ሆኗል፡፡
ሜላት በሀገራችን ልዩና ዘመናዊ የሆነ የሽቶ ፋብሪካ በመክፈት ምርቶቿን በስፋት በማምረት አንዲሁም ለሌሎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡
📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





6 comments
እህትማማቾች ናቸው?
ሜሉዬ እንኳን ለዚህ አበቃሽ
ብዙ ስብራቶችን አልፈሽ ነው ለዚህ ክብር የበቃሽው
ማርያም ባለሽቶዋን አስታወሰኝ
ትርፉ ለፋኖ ጥይት መግዣ ነዉ🤔
ደህና አድርጎ የሚቾምሳትን መምረጧ ልክ ነው
መንሱርን ማረግ ነበረባት