banner

7 ሚሊዮን ብር የወጣበት የድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ የመጀመሪያ አልበም ሊወጣ ነው።

#FastMereja
”አያንቱ” የተሰኘው የድምፃዊ አንዷለም ጎሳ የመጀመሪያ አልበም በውስጡ 16 ዘፈኖችን ያካተተ ሲሆን፣ 16 ቱ የሙዚቃ ስራዎች የሀገራችንን የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን ተጠቅመው የቀረቡ ናቸው ተብሏል።

አዲሱን አልበም ምክንያት በማድረግ ዛሬ መስከረም 8/2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አልበሙ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የተውጣጡ 6 የባህል ሙዚቃ ዘፈኖችን እንዲሁም ፣ 10 ተከታታይ የፈጠራ (experimental ) ዘፈኖች እንዳካተተ ነው የተገለፀው።

ይህ አያንቱ የተሰኘው የሙዚቃ አልበም ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆንና እና በአለም አቀፍ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ብዙ ሙዚቀኞችን እና ባለሙያዎችን አሳትፏል።

ከእነዚህም መካከል ኤፍሬም ብርቅነህ፣ ሚኪ ጃኖ፣ እዮብ ባልቻ፣ አንተነ (አቡዝ) እና ኤንዲ ቤተ ዜማ በሙዚቃ ቅንብር ተሳትፈዋል።

እንዲሁም በታዋቂው የሙዚቃ ባለሙያ አበጋዝ ሾይታ ማስተር የተደረገ ሲሆን ፤ በLive Instrument መሳሪያ ፣ ሉአም ማሃሪ፣ ሮቤል ማሃሪ፣ ዘርይሁን እና ቻፒ ተሳትፏል።

በግጥም እና ዜማ ዘርፍ ላሊሳ ኢንድሪስ፣ አቦማ ማርጋ ፣ አርቲስት አቢራሂም መሀመድ፣ ሞቲ አባ ዳሌ እና ፋጤ አኒያ፣ ናሆም መኩሪያ፣ ኢፊረም ብርቅነህ፣ ዘርዓ ብሩክ እና ኢሳያስ ተሳትፈዋል።

አርቲስት አንዱአለም ጎሳ የሙዚቃ አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከ6 አመታት በላይ ፈጅቶበታል።

ይህንንም ስራ ለማጠናቀቅ በአጠቃላይ 7 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ገደማ ፈጅቷል።

አልበሙ መስከርም 12/2017 ዓ.ም በሁሉም የሙዚቃ platforms ላይ የሚለቀቅ ሲሆን ።

የአያንቱ አልበም ምርቃት ዝግጅትን በተመለከተ ፤ እሁድ መስከረም 12 ቀን 2017 ከቀኑ 10 ሰዐት በስካይ ላይት ሆቴል አርቲስቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ወዳጆች በተገኙበት ይካሄዳል ። የሙዚቃ አልበሙ ምረቃ ዝግጅት ላይ አርቲስት አንዱአለም ጎሳ 2 አዳዲስ ስራዎች በመድረክ ላይ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ታዋቂ እና አንጋፋ አርቲስቶች ስራቸውን በማቅረብ መድረኩን እንደሚያደምቁት ተነግሯል።





Leave a Comment