0
#FastMereja
ድምፃዊ ሮፍናን ኑሪ በአንድ ባለሃብት ላይ ክስ መሰረተ። ተከሳሽ አቶ ኃይለስላሴ አስረስ ሲባሉ ከሮፍናን 6 ሚሊዮን ብር ተቀብለው ባለመመለሳቸው እንደሆነ ፋስት መረጃ ከኢትዮጲካሊንክ ሰምቷል።
ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ያደርጋሉ። በስምምነቱ መሰረት ሮፍናን የአቶ ኃይለስላሴን መኖሪያ ቤት በ165 ሚሊዮን ብር ለመግዛት ተስማምተው 6 ሚሊዮን ብር በተለያየ ጊዜ ቀብድ ሮፍናን ለአቶ ኃይለስላሴ መክፈሉን ኢትዮፒካሊንክ የክሱን ፋይል ጠቅሶ ዘግቧል።
አቶ ኃይለስለሴ ከስምምነቱ በኋላ ለሌላ ሰው በ170 ሚሊዮን ብር ቤቱን ሸጠውታል። የተከፈለ 6 ሚሊዮን ብር እንዲመልሱልኝ በተደጋጋሚ ብጠይቅም ዛሬ ነገ እያሉ ብሩን አዘገዩት ስለዚህ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዤ በመሄድ ነሃሴ 6/2016 ዓ.ም ክስ መስርቻለሁ ብሏል።
አቶ ኃይለስላሴ የወሰዱትን 6 ሚሊዮን ብር እና 9% ወለድ እንዲከፍሉኝ ሲል ነው ክስ ውስጥ የገባው።

1 comment
ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ 🙄