banner

ለታጋቾች ማስለቀቂያ ብር ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች እራሳቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰማ።

ከሳምንት በፊት በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ 38 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን አዲስ ማለዳ ከአይን እማኞች ሰምታ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከ250ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎም አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘቡን ለመክፈል ወደ ተባሉበት ቦታ ማቅናታቸውን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች ገንዘብ አቀባዮቹ በቦታው ሲደርሱ ግን እራሳቸው በታጣቂዎቹ መታገታቸውን ነው የገለጹት ፡፡

‹‹ካሉበት ቦታ ሆነው ስልክ ደውለው እኛም ታግተናል›› አሉን የሚሉት አንድ ምንጭ የታገቱትን አስፈትተው ይመጣሉ ብለን ተስፋ ስናደርግ እነሱም መያዛቸው ሌላ ጭንቀት ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡

ታጋቾችን ለማስለቅ የሚያስችል ገንዘብ አሁን ላይ እንደሌላቸው የሚገልጹት እነዚህ የታጋች ቤተሰቦች የቀደሙትንም ለማስፈታት በገበያ ቦታ፣ በእድርና በመሰል ማህበራዊ አደረጃጀቶች በኩል ጥረት ተደርጎ ገንዘቡ እንደተሰበሰበ ገልጸዋል፡፡

መንቀሳቀስና መስራት ውድ እየሆነ መጥቷል፤ መንግስትም የህግ የበላይነት የሚባለውን መሰረታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በማለትም አካባቢው ላይ የሚታይ ስጋት አሁንም እንዳለ ነው ያስታወቁት፡፡

በሌላ በኩል ታግተው ከነበሩ 38 ሰዎች ውስጥ 5 ያህል ታጋቾች ማምለጣቸውንም እነዚህ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ምንጮች አሁን ላይ ያመለጡት ታጋቾች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

የሸኔ ታጣቂ ቡድኖቹ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ከጎቤሳ ከተማ ወደ ተለያዩ ከተሞች በመጓዝ ላይ የነበሩ አጠቃላይ 8 የህዝብ ማመላለሻዎችን ጋለማ በሚባል ጫካ ውስጥ በማስቆም 38 ሰዎችን በመምረጥ ማገታቸው የሚታወስ ነው።

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ ከክልሉ መንግስት ተደጋሚ ምላሽ ለማግኘት ለሳምንታት ያደረገቸው ጥረት አልተሳካም፡፡

Via: አዲስ ማለዳ

10 comments

Berry Adane September 19, 2024 - 9:28 am

ቀልድ ነው በሉን!!

Reply
Firew Bekele September 19, 2024 - 9:29 am

ወዩ🤭🤭

Reply
Alelign Tegbu September 19, 2024 - 9:31 am

አጋቹ መንግስት ነው።

Reply
አሪፍ አይቸኩልም September 19, 2024 - 9:33 am

Shene adelem mengst new agachu😂😂😂

Reply
ሲሆን ይሆናል September 19, 2024 - 9:33 am

በቃ ይሄ ብሄር ምንም ሃገር እሚመራ አይወጣበትም

Reply
Yohannes Seyoum September 19, 2024 - 9:35 am

አይ ሃገሬ እንዲ ትሁን

Reply
Dejene K Abera September 19, 2024 - 9:35 am

የሄዱት ሰዎች ታግተናል ብለው ከደወሉ አጋቾቹ እራሳቸው መሆን አለባቸው…ስልክ እንድትደውል የሚፈቅድ አጋች???

Reply
Ephirem Shofe September 19, 2024 - 9:35 am

በኔ ስልጣን ዘመን ማንም አጋች እና ታጋች አይኖርም ብሎ ነበረ

ዐቢይ

Reply
Fetu Shifa Siraj September 19, 2024 - 9:36 am

ሰውለሰው ድረማ

Reply
Tolina Tube September 19, 2024 - 9:37 am

አያድርስ ነው😰

Reply

Leave a Comment