banner

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የኦሎምፒክ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴን አገደ

#FastMereja
መስከረም 8 2017 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 333122 የዋለው ችሎት በይግባኝ ባዮች በእነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ (4 ሰዎች) እና መልስ ሰጪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (5 ሰዎች) ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ባዮች በዋናነት ያነሱት

– ግንቦት 5 2016 እና ሰኔ 4 2016 የተከናወኑ ህገወጥ የጠቅላላ ጉባኤ እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ እንዲታገድ

– የህዝብ እና የሀገር ሀብት እንዳይባክን ከደመወዝ ክፍያ ውጪ የባንክ አካውንት እንዲታገድ ጠይቀዋል

የይግባኝ መነሻቸውን ፍርድ ቤቱ የመረመረ ሲሆን አመልካቾችና ጠበቆች በሰጡት ምልሽ በዋናነት ህግና ስርዓት ተከብሮ ተቋሙን የመታደግ አላማና ወደነበረበት ከፍታ ለመመለስ ከመሻት የመነጨ ፍላጎት እና ቁጭት እንጂ የጥቅምም ሆነ የስልጣን ፍላጎት እንደሌላቸው ለፍርድ ቤት አስረድተዋል፡፡

በስራ ማስኬጃ ሰበብ ብክነት እንዳይኖር እንዲሁም በሪፎርም በሚል ምክንያት የታቀዱ ብክነቶች ስለመኖራቸው መረጃ ስላለን ፍርድ ቤቱ አካውንቱን እንዲያግድ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ትእዛዝ ለባንኮችና ለዋና መስሪያ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

ሌላኛው ትእዛዝ ለኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በቀን 04/10/2016 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ የታገደ መሆኑን እንዲያውቁና እግዱን እንዲፈፅሙም ታዟል፡፡

የመልስ ሰጪዎችን ምላሽ ለመስማት ለመስከረም20 ፍርድቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

10 comments

ዘሩ ቀለጠ September 19, 2024 - 12:22 pm

መቼ በተፈረደ ፍርድ ላይ ነው ይግባኝ ተጠይቆ እግድ የታገደው ? ኧረ ባካችሁ የህግ ቃላት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ አድርጉ🙄

Reply
ዮሐንስ ዘየካ September 19, 2024 - 12:23 pm

አሸበር በለመደው ስከሳው ሃገር አስቀጣለው ማለቱ አይቀርም የስርአቱ መግማማት ማሳያ እከክ የሆነ ሰውዬ

Reply
Kalkidan Dawit September 19, 2024 - 12:25 pm

ሀይሌ ግን ይመቸው፣ ይሄን ተቋም ከውድቀት እየታደገው ነው

Reply
Amare Haile September 19, 2024 - 12:26 pm

ጀግና ሃይሌ ሚገርም ስራ 💪 በርታ ከጎንህ ነን

Reply
Stupidity Craziness Endless September 19, 2024 - 12:26 pm

ፓፓፓ confuse and convince.

Reply
Habtsh Endale September 19, 2024 - 12:29 pm

ሀገሪቷ መቀጣቷ እርግጥ እየሆነ ነው

Reply
Eldana Seyum September 19, 2024 - 12:31 pm

አሸብር be like “ፈጣሪ ሆይ ያገዱት የ facebook አካውንቴን ነው በለኝ”
😲

Reply
Hailu WM September 19, 2024 - 12:33 pm

አዎን ፍትህ መኖሩንም ጋጠወጦቹ ይወቁት ኢትዮጵያም ሀገር ሀገር ትሽተት እንጂ ጎበዝ!!!!!

Reply
Wuletaw Tesfaye September 19, 2024 - 12:33 pm

ሀገርን ለማዋረድ የተፈጠረው ማፍያ ቡድን ላይ ብቻውን መንግሥት ሆኖ የተገለጠው ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስለሴ 👊👊👊

Reply
Tsegaye Feru September 19, 2024 - 12:36 pm

የቅጣት ዉሳኔ ይጠበቃል

Reply

Leave a Comment