0
#FastMereja
ሂል ቦተም ፕሮፐርቲስ በአያት አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኘውን በዘመናዊ መልኩ የተገነባ ባለ 12 ፎቅ ሶስት መኝታ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ መስከረም 11/2016 ዓ.ም አስመርቋል።
የመኖሪያ አፓርትመንቱ በግቢው ውስጥ ጅም፣ ስፓ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የቴኒስ ሜዳ፣ በቂ የመኪና ማቆሚያ ዘመናዊ አሳንሰር ከመጠባበቂያ ጀኔሬተር ጋር ያሟላ እንደሆነ ተነግሯል።
በዚሁ በተጠናቀቀው አፓርትመንት ግቢ ውስጥ ሁለተኛውን ብሎክ አፓርትመንት በመገንባት እና በመሸጥ ላይ ሲገኝ በተጨማሪም በአይነቱ ለየት ያለ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንት በመሀል ካዛንችስ አዲስ ግንበታ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ተገልጿል።
ሂል ቦተም በመዝናኛ ማዕከልነቱ ለ16 ዓመታት ህብረተሰቡን በማገልገል የሚታወቀው ሲሆን የህበረተሰቡን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በሪል ስቴቱ ዘርፍ በሰፊው በማሰማራት ራዕዩን አንግቦ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተነግሯል።
📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





1 comment
ህብረተ ሰቡን ማለት ግን ምን ማለት ነው ?