banner

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “የክልሉ የጸጥታ አካላት በስሬ ሁነው እየተመሩ ይሰራሉ” ሲል አስታወቀ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም አካሄድኩት ባለው መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ በመምከር ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ይፋ አድርጓል፤ ከውሳኔዎቹ መካከልም በክልሉ የሚገኙ “የጸጥታ አካላት እንደ አንድ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል” መሆናቸውን ጠቁሟል።

“አግባብነት ባለው ጥናት እና ምክክር እየተደረገበት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት እና በካቢኔው እየተመሩ በህግ እና በስርአት ተልዕኮ እየተሰጣቸው ይፈጽማሉ” ሲል አስታውቋል።

በትግራይ ክልል የተፈጠረው ችግር በህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ተደርጎ እየቀረበ ያለው ነገር ፍጹም የተሳሳተ እና የችግሩ ተወናዮች እንዲሁም አሰላለፋቸውን በሳተ መልኩ የቀረበ መሆኑን ህዝቡ በግልጽ ሊያውቅ ይገባል ብሏል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎቹን እና እንቅስቃሴዎቹን ለማሳለጥ ይረዳው ዘንድ በተለያዩ እርከኖች የሚያካሂደውን የሃላፊነት ምደባ እንደሚቀጥልበትም አስታውቋል፤ ይህ እንዳይካሄድ በማንኛውም መልኩ እንቅፋት በሚፈጥሩ አካላት ላይ በህጋዊ መንገድ መልክ ለማስያዝ እሰራለሁ ሲል ገልጿል።

Via Addis Standard

10 comments

Endalew Tarekegn September 23, 2024 - 9:47 am

እናንተም እዲህ መሆናቹህ በጣም ያሳዝናል!!

Reply
The Entrpreneur September 23, 2024 - 9:47 am

መንግስትና ፓርቲ እንዲህ ሲለያይ ደስ ይላል።

Reply
Miki Shekspir September 23, 2024 - 9:48 am

አንበሳ ጌች ሳኒታይዘር 👌

Reply
Selam Selam September 23, 2024 - 9:51 am

ለምንድን ነው የሚመሩት? ወይስ አይናቸው ላይ ችግር አለ???

Reply
ያማል ቅኔው September 23, 2024 - 9:52 am

ከጸትታው አካላት አንዱ መከላከያውም አለበት እናስ መከላከያውንም ማዘዝ አለብኝ እያለ ነው ?

Reply
Tofa Man September 23, 2024 - 9:55 am

አወዛጋቢው ☺☺☺☺

Reply
Wubetu century metal works September 23, 2024 - 9:57 am

ገና መከላከያ በስር ይሆናል 😁

Reply
Feven Hailemichael September 23, 2024 - 10:04 am

ወይ ፍርሃት፣ ማዘዝ ነው እንጅ ምንድን ነው ማሳወቅ 😂😂😂

Reply
Kibru Doge September 23, 2024 - 10:35 am

TPLFም ጭምር ነው በለኝ🙏😂

Reply
Habtamu Kidane September 23, 2024 - 10:35 am

ታዲያ በፊት በማን ተመርቶ ነው ሲሰሩ የነበሩ?

Reply

Leave a Comment