banner

“የጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ሰራዊትን በስሩ በማድረግ ማዘዝ አይችልም” ሲል በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት አሳሰ

“የጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ሰራዊትን በስሩ በማድረግ ማዘዝ አይችልም” ሲል በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት አሳሰበ

“በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያሉ መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት ወደ ተግባር እገባለሁ” ሲልም አስታውቋል።

በደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በትላንት መስከረም 14 መግለጫው “ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስሙ እንደሚያመለክተው አስተዳደራዊ ስራዎችን እያከናወነ በአጭር ግዜ እንደመሸጋገሪያ የሚያገለግል እንጂ የትግራይ ሰራዊትን በስሩ አድርጎ በዕዝ ሰንሰለት ለመምራት የተሰጠው ተልእኮ፣ መዋቅርም ሆነ አደረጃጀት የለውም” ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም አሁን ባለው አደረጃጀት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግስቱ መሆኑን ያመላከተው መግለጫው የትግራይ ሰራዊት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስር እንዲሆን ማድረግ ማለት “በስልጣን ሰንሰለታዊ ግንኙነት በፌደራል መንግስቱ ስር በማስገባት ማንኛውንም ትዕዛዝ እንዲቀበል የሚያደርገው አደገኛ አደረጃጀት የሚያስይዘው ነው” ሲል አስታውቋል።

“በአሁኑ ወቅት ክልሉ ያጋጠመው ችግር በህወሓት ውስጥ ያለ ችግር ብቻ አድርጎ ለማቅረብ እየተደረገ ያለው ጥረት ተቀባይነት የለውም” ሲል አስታውቆ “ኢህአዴግን ከውስጥ እንዳፈረሱት ሁሉ አነዚህ ሀይሎችም በህወሓት ውስጥ ሁነው ፓርቲውን ለማፍረስ ቢጥሩም ስላልተሳካላቸው አሁን ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ተሸፍነው እየተንቀሳቀሱ ነው” ሲል ኮንኗል ሲል አዱስ ስታንዳርድ ነው የዘገበው።

2 comments

ምን ነካሽ ሀገሬ September 25, 2024 - 9:57 am

ወያኔ ሙታለች ያውም ገምታ በስብሳ እየተቆራረጠች ። የስራችው ክፋትን ሁሉ ተጎንጭታ ስለዚ ለሞት ነገር ግዜ አንሰጥም የራሳቸው ጉዳይ

Reply
Dawit Ab Link September 25, 2024 - 9:58 am

ባንክ ቤት እንዳስቀመጡት ገንዘብ የኔነው የኔነው

Reply

Leave a Comment