banner

የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን ዶ/ር አሸበር ወ/ጊዮርጊስን እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን በሙስና እና ህገወጥ የሰው ዝውውር ሊከስ

የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን ዶ/ር አሸበር ወ/ጊዮርጊስን እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን በሙስና እና ህገወጥ የሰው ዝውውር ሊከስ ነው።
#FastMereja

የአለም አቀፉ እና በኢትዮጵያዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም በአለም አቀፍ እንዲሁም በአፍሪካው የቦክስ ተቋማት እና በኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ዙሪያ ስለተሰራጩ መረጃዎች የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዛሬ መስከረም 16/2017 ዓ.ም መግለጫ ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕረዝደንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “የአለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ- IOC የኢትዮጵያ ቦክስ ኮንፌደሬሽንን EOC -አግዶታል፤ እኛም እንድናግድ ታዘናል፤ እኛም እውቅና ከልክለነዋል፤ የቦክስ ፌደሬሽኑን አፍርሰን እስከ ኖቨንበር 4 ድረስ አዲስ ፌደሬሸን እንመሰረታለን፤ ይህንንም የማድረግ ስልጣን ለኛ ተሰቶናል» ያሉትን ንግግር አስመልክቶ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን AFBC እና የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን EBF ምላሽ ሰጥቷል።

አቶ ዳዊት ዋስይሁን የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን የኮሙኒኬሽን ኃላፊ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕረዝዳንት ዶ/ር አሸበር የቦክስ ፌደሬሽኑን አፍርሰን አዲስ እናቋቁማለን ያሉት ለሶስተኛ ጊዜ የተመረጠው የኮሚቴው ፕረዝዳንትም ሆነ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህ ስልጣን እና ኃላፊነት የላቸውም ብሏል።

የኦሎምፒክ ኮሚቴው ስራ አስፈፃሚ እና ፕረዝዳንት ህገወጥ ሆኖ ሳለ፣ መቶ ሚልየን ብሮች የት እንዳስገባ ባልታወቀበት ሁኔታ እና የክስ ሂደት ላይ ሆኖ ሳለ፣ ስራ አስፈፃሚው እና ፕረዝዳንቱ ከ2 ጊዜ በላይ መመረጥ እንደማይችል የህግ ማዕቀፍ ያለው ቢሆንም ይህን ሽሮ እና በህገወጥ መንገድ ደንብ አሻሽሎ የተመረጠ ህገወጥ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የአሸናፊነት እና አንድነት መገለጫ የሆነውን ኦሎምፒክ ያለ ውጤት ያስቀረ ውጤት አልባ ሆኖ ሳለ ህጋዊ ተቋምን አፍራሽ እና ተቺ ሆኖ መቅረቡን የምናወግዝ መሆኑን እንገልፃለን ሲሉ አቶ ዳዊት በመግለጫቸው ተናግሯል።

የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ፕረዝዳንቱ ከፍተሐብሔር ክሱ በተጨማሪም በሙስና እና ህገወጥ የሰው ዝውውር እና ሌሎች የወንጀል ክሶች በቅርቡ እንደሚቀርብበት ተገልጿል።

የኦሎምፒክ ኮሚቴ የቦክሱን ፌደሬሽን የማፍረስም ሆነ አዲስ የማቋቋም ስልጣንም ሆነ መብት እንደሌላቸው የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን በመግለጫው ገልጿል።



3 comments

ቻው ቼልሲ September 26, 2024 - 1:49 pm

አሼ አይሰማህም 😂😂😂

Reply
Miftah Kalid September 26, 2024 - 1:50 pm

ሀይሌገብረስላሴ የአሸብርን ስም ለማጥፋት ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልገባበት ጉድጓድ የለም። እሄ ከሀይሌ አይጠበቅም።

Reply
Nuredin Seid September 26, 2024 - 1:59 pm

የቦክስ ፌዴሬሽንን እየመሩ የምን መለማመጥ ነው ዶ/ር አሸብርን እና ኮሚቴውን በቦክስ መዘረር አቅቷችሁ ነው ? የምትለማመጧቸው?🤔🤔🤔🤔

Reply

Leave a Comment