banner

ጋሞ ዞን ያልተጠቀመበት ቢራ ፋብሪካዎች የነገሱበት ዮ ማስቃላ በዶርዞ

#FastMereja
እለቱ መስከረም 16/2017 ዓ.ም ፋስት መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ተገኝተን ነበር… ጉዞ ወደ ዶርዞ መንደር፣ ከአርባምንጭ ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኘው በተራራ ላይ የምትገኘው ዶርዞ መንደር መስከረም 16 በአንድ ቦታ እስከ 2000 በሬ የሚታረድበት የዶርዞ መንደር ነው።

መንገዱ የተወሰነ አስፋልት ንጣፍ ሲኖረው ከዛ በኋላ ፒስታ መንገድ ነው። መንገዱ ተራራማ በመሆኑ ጉልበት ያለው መኪና ያስፈልጋል። መንገዱን ወደ አስፋልት ለመስራት እንቅስቃሴ እንዳለ ተነግሮናል። በመንገዳችን ላይም የተወሰኑ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ጎብኚዎች ወደ ዶርዜ ሲጓዙ ተመልክተናል።

ለፋስት መረጃ የመጀመሪያ የሆነው የዶርዜ መንደር ጉብኝት አረንጓዴውን ተራራ አቆራርጠን ዶርዜ ደርሰናል። በርካታ የዶርዜ ነዋሪዎች ዮ ማስቃላን ለማክበር በአዳዲስ ልብሶች እና በባህላዊ ልብሶች የዶርዜን መንደር የበዓል ድባብ አልበሰዋታል።

የበሬ ቅርጫ በመደብ ተደርጎ እንደ ሽንኩርት እና ድንች ሲሸጥ ተዟዙረን ተመልክተናል። ተዘዋውረን እንደተመለከትነው በሀገራችን የሚገኙ የቢራ ፋብሪካዎች የራሳቸውን ቦታ እና የራሳቸውን የሙዚቃ ባንድ ይዘው ቢራ እየሸጡ ዮ ማስቃላን “የቢራ ፌስቲቫል” አስመስለውታል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በድንገት የተገኘ ሰው የቢራ ባዛር ሊመስለው ይችላል። ቢያንስ የጋሞ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ይህን ትልቅ ሃብት እንደ ቢራ ፋብሪካዎቹ የራሱን ቦታ በመያዝ ስለ ዮ ማስቃላ ፕሮሞት የሚያደርግበት መድረክ ሊኖረው ይገባ ነበር። አልተመለከትንም ካለም በቢራ ፋብሪካዎቹ ተበልጧል።

የዞኑ መስተዳደር ሌላኛው ድክመት ስለ ዮ ማስቃላ በዶርዞ መንደር አከባበር በደንብ ፕሮሞት በማድረግ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ወደ ጋሞ ዞን እንዲጎርፉ ማድረግ አልቻለም። ለማስተዋወቅ ፋስት መረጃ ዝግጁ ነው። እኛ ዛሬ ተገኝተን ይህ ትልቅ ሀብት በቢራ ፋብሪካዎች ባህሉ ሲደበቅ ተመልክተናል።

በቀጣይ አመታት ጋሞ ዞን ዮ ማስቃላን ባህሉን በጠበቅ መልኩ የቢራ ፋብሪካዎች ሳይሆን ዮ ማስቃላ እና የዶርዜ መንደር ጎልተው የሚታዩበት አከባበር እንደሚሆን እንደ ፋስት መረጃ ተስፋ አለን።

ቀጣይ ጉብኝት የዶርዜ ቪሌጅ ነው። በአቶ መኮንን ወይም ሁሉም በሚጠራው በሞኬ አስጎብኚነት በዶርዜ ቪሌጅ ተገኝተን ስለ ቤቶቹ አሰራር ማብሪያ ተደርጎልናል፣ ስለ እንሰት ሰፊ ማብራሪያ አግኝተናል ዮ ዮ ዮ ብለን በዶርዜ ቪሌጅ ስለ ዶርዜ ከባህል እና ቱሪዝም ያጣነው በሞኬ አግኝተናል።

ሞኬ በቪሌጁ እየተዘዋወረ ብሉልኝ ጠጡልኝ በማለት ጎበዝ ደጋሽ መሆኑን አሳይቷል፣ ዶርዜ ባህላዊ መንደር ሰው ሳይበዛበት ብቻውን በተረጋጋ ሁኔታ በቀጣይ መጎብኘት ያለበት አከባቢ ነው ዶርዜ መንደር ሞኬ ጋር እንመለሳለን።

በዶርዜ ጥሬ ስጋ ተበላ ሳይሆን እንደ ውኃ ተጠጣ ነው የሚባለው። ከዛ ዮ ዮ ዮ ዮ ዮ ዮ ዮ

ቸር እንሰብት
ፋስት መረጃ ከጋሞ ዞን ዶርዜ





Leave a Comment