banner

መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው ከአራት 4 ቤተሰባቸው ጋር ተገደሉ።

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ( ሞጆ ) ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትኅትና ሲያገለግሉ የቆዩት መልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ለጊዜው ባልታወቁ ኃይሎች በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የገለጸ ሲሆን ልጃቸው ዲ/ን መልአክ ወልደ ኢየሱስ የአባቱን ፈለግ በመከተል በዲቁና የሚያገለግል ነበር፡፡

ጸሎተ ፍትሐት ሥርዓቱም በብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እየተመራ ፡ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፡ አበው ካህናት ሊቃውንት ፡ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተከናውኗል።

Via: ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ




6 comments

Selam Selam September 27, 2024 - 1:06 pm

😭 አይ ኢትዮጵያ

Reply
Tigistu Alex September 27, 2024 - 1:07 pm

ወዮ ይህች ናት ሃገሬ??

Reply
Mike Kt September 27, 2024 - 1:08 pm

እግዚአብሔርም ጨከነብን እኮ

Reply
Mesay Bay September 27, 2024 - 1:09 pm

እንዲሕ አይነቱ ዘር ተኮር ግድያ ነብስ ይማር አዝነናል በሚል መታለፍ የለበትም።የሆነ ቦታ ላይ ማስቆም መቆም አለበት ። እስከመቸ ለቅሶ?መንግስት አለሑ ይል ይሆን? ሲኖዶሱስ?😭😭😭😭😭😭

Reply
Chaltu Regasa September 27, 2024 - 1:09 pm

Maninetachew baltaweke gedayochun waga atasatu be gils adelinde endemigedlu eyenegeru yemiardut

Reply
አዲስ ፋና September 27, 2024 - 1:10 pm

ፈጣሪ ሆይ ይቅር በለን ምን አይነት ጊዜ ደረስን አቤቱ በቃ በለን ነብስ ይማር አባታችን😢

Reply

Leave a Comment