banner

እስራኤል ከባለፈው ሰኞ እለት ጀምሮ ሊባኖስ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ700 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

እስራኤል የአሜሪካ ቦምቦችን ተጠቅማ ቤሩትን እየደበደበች ነው ስትል ኢራን ከሰሰች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ እስራኤል አሜሪካ ሰራሽ የሆኑትን በርካታ “በንከር በስተር” ቦምቦቸን በመጠቀም በትናንትናው እለት ቤሩትን ደብድባለች ሲሉ ከሰዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ዛሬ ጠዋት የእስራኤል አገዛዝ በአሜሪካ የተሰጡትን 5000 ፓውንድ ክብደት ያላቸውን በንከር በስተር ቦምቦችን ተጠቅሞ በቤሩት የመኖሪያ መንደሮችን ደብድቧል” ሲሉ በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ለተሰበሰበው የተመድ የጸጥታው ምክርቤት ተናግረዋል።

እስራኤል በትናንትናው እለት በቤሩት ዳርቻ በሚገኘው የሄዝቦላ ዋና ማዘዣ ጣቢያ ላይ ጥቃት የሰነዘረችው የቡድኑን ዋና አዛዥ ለመግደል ነበር። ነገርግን የቡድኑ መሪ የሆነው ሰኢድ ሀሰን ነስረላህ መገደሉን ለማረጋገጥ ጊዜው ገና መሆኑን ከፍተኛ የእስራኤል ባለስልጣናት ተናግረዋል።

እስራኤል ከባለፈው ሰኞ እለት ጀምሮ ሊባኖስ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ700 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በመቶሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ከቤታቸው ተፈናቅለዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት በተካሄደው የተመድ 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ እስራኤል ከኢራን ጋር እየተዋጋች መሆኗን ተናግረዋል።

እየተዋጋን ያለነው ሊያጠፉን ከሚሹ “አረመኔ ጠላቶች ጋር ነው” ያሉት ኔታንያሁ “እስራኤል ኢራን በከፈተችው 7 አውደ ውግያዎች እየተዋጋች ትገኛለች፤ ተሄራን ከምታሰማራቸው ርህራሄ የለሽ ገዳዮች እራሳችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን”ብለዋል።

ኔታንያሁ “በኢራን ውስጥ የእስራኤል ረጅም ክንድ የማይደርስበት ቦታ አለመኖሩ ሊታሰብበት ይገባል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሊባኖስ የጀመረችውን ጥቃት እንድታቆም ጫና ቢደረግባትም፣ ከጋዛ ወደ ሊባኖስ ትኩረቷን ያደረገችው እስራኤል ተፈናቃዮችን መመለስን ጨምሮ ሁሉም ግቦቿ እስከሚሳኩ ድረስ ማጥቃቷን እንደምትገፋበት ገልጻለች።

የሊባኖስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደላ ቦሀቢቢ ግን ተኩስ አቁም መድረግ እንዳለበት አሳስበል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ተኩስ አቁም የማይደረግ ከሆነ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ሰላም እና አለመረጋጋትን አደጋ ውስጥ የሚያስገባ አደገኛ ቅርቃር ሊፈጠር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አሜሪካ እና የአውሮፓ ባለስልጣናት ለ21 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ሀሳብ አቅርበዋል።

ዘገባው የዐል ዐይን ነው።

10 comments

Emmanuel Negn September 28, 2024 - 8:43 am

ድል ለእስራኤል

Reply
Tamagn Teshome September 28, 2024 - 8:44 am

እስራኤል ግን 😥😭

Reply
Ybe Ye Nebert Lij September 28, 2024 - 8:44 am

Nice work

Reply
Tesfa Selam September 28, 2024 - 8:45 am

አርፈው አይቀመጡም ነበር ሽርጣሞች

Reply
Bin BA September 28, 2024 - 8:46 am

ከነብሰ በላ ሌላ ምን ይጠበቃል

Reply
Selena September 28, 2024 - 8:46 am

ምን አይነት ሀያል ሀገር ነች ግን እስራኤል

Reply
Wude Wako September 28, 2024 - 8:47 am

Israel 💪

🇱🇧✌😂😭

Reply
Madebo Girma September 28, 2024 - 8:47 am

አስቸዃይ መፍትሄ የሚያስፈለገው የሊባኖስ ጉዳይ።
የረጅም አመታት ቂም ከሰሞኑ በሊባኖስ ምድር ላይ ፈንድቷል።
እስራኤል እና ሊባኖስ (ሄዝቦል) ከሰሞኑ በእሳት መጫወት ጀምረዋል። ሂዝቦላን ከሊባኖስ ምድር ካላጠፋሁ ወደ ኋላ አልልም ያለችው እስራኤል እሳት በማዝመት ሊባኖስን በቦምብ እና ተምዘግዛጊ ሚሳኤል መደብደብ ከጀመረችበት ገና በሁለት ቀን ውስ ወደ አንድ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፣ በመቶ ሺዎች ተፈናቅለዋል።
አሳሳቢው ጉዳይ ታዲያ ቤሩት እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ጉዳይ ነዉ። በቀላሉ እስከ 300ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያን በሊባኖስ እንደሚኖሩ ይታወቃል። ኑሮአቸውን ለመለወጥ ብሎም ቤተሰብ ለማገዝ ከአገር የተሰደዱት ኢትዬጲያውያን በሰቆቃ ላይ እንደሚገኙ በጆሮዪ ስምቻለሁ። በርካታ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ማሰማት ላይ ቢገኙም እስከ አሁን ድረስ ዞር ብሎ ያያቸው እንደሌለ ነዋሪዎች እምባ እየተናነቃቸው በጆሮዬ ነግረውኛል። እንዲያውም የሚያስገርመው ነገር በቤሩት ያለው ቆንፅላ ፅ/ቤት ለአዲስ አመት በዓል ለማክበር በሚል ምክኒያት ቢሮውን ከዘጋ 20 ቀን እንዳለፈው ነው የሚናገሩት። በርካታ ኢትዬጲያውያን የሚኖሩበት ቤሩት ከትናንት ጀምሮ ተጠናክሮ በቀጠለው ድብደባ ስንት ሰው እንደሞተ እንዃን ለማወቅ አልተቻለም። በርካታ አገራት ዜጎቻቸውን እያሰወጡ ባለበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ምን እስኪመጣ ነው እየጠበቀ ያለው? ለዜጎቻችን እንድረስላቸው ድምፃችን እናሰማ። Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) Elias Meseret BBC News Amharic Ethiopian Reporter Ethiopian Broadcasting Corporation #ውጭጉዳይሚንስትር Abiy Ahmed Ali Ergogie Tesfaye Muferihat Kamil Ahmed Ethiopian Human Rights Commission Daniel Bekele @Ministry of ForeignAffairs Ethiopia

Reply
Sintayehu Birhanu September 28, 2024 - 8:47 am

ከእስራኤል ዓይን የምሰዉር ምንም ነገር አይኖርም ✌️

Reply
Eyerus Eyu September 28, 2024 - 8:47 am

እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነውና ሰላሙን ያውርድላቸው 💔😢

Reply

Leave a Comment