የሀሰን ናስረላ መገደል እርግጥ የሆነ ይመስላል። ላለፉት 30 ዓመታት የሄዝቦላ መሪና የፀረ እስራኤል ንቅናቄ ምልክት ሆኖ የኖሩት ሼህ ሰይድ ሀሰን ነስረላ ከእንግዲህ የሉም።
በርግጥ ሁሉም ሊባኖሳዊ የሳቸው ደጋፊ አይደለም። እንዳውም ከሺያ ሙስሊሞች ውጭ ያሉት በባላንጣነት ይመለከቷቸዋል። አንድ አገር ውስጥ ሁለት ሰራዊት እንዲኖር በማድረጋቸው፣ የኢራንን ተፅዕኖን ወደ ሊባኖስ ፖለቲካ በመምጣታቸው፣ በሶሪያም ለበሸር አላሳድ መንግስት ወታደር ልኮ በመፋለማቸው እና በሌሎች ጉዳዮችም በሱኒ ሙስሊሞች እና በክርስቲያኖች አይወድዱም። ለሊባኖስ ሳይሆን ለሺያዎች ብቻ የቆሙ ናቸው ይላቸዋል። በርግጥ በደቡብ በኩል እስራኤል የአገሪቱን ድንበር ለቃ እንድትወጣ ጫና በመፍጠር እና ድንበሩንም በመጠበቅ ባስመዘገቡት ውጤት በመላው አረብ ተሰሚነትን አግኝተዋል።
የመካከለኛው ምስራቋ ፈረንሳይ ስትባል የነበረችው..ሽቅርቅሯ… የባህር ደርቻዋ… ሊባኖስ በብዙ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና በኢኮኖሚያዊ ድቀት የመከራ ዘመን ውስጥ ናት። ፖለቲካዊ ክፍፍል፣ በየጊዜው የሚቀያየር ደካማ መንግስት፣ የኑሮ ውድነት፣ ስራ አጥነት…መገለጫዎቿ ከሆኑ ሰነባብቷል።
ከእርስ በርስ ጦርነት በኃላ መተግበር የጀመረው የስልጣን ክፍፍል ቀመርም ለአገሪቱ ጠንካራ መንግስት አላስገኘም። በቀመሩ መሠረት ርዕሰ ብሄሩ (ፕረዚዳንቱ) ከክርስቲያኖች ሲሆን፣ ከሳውዲ ቡራኬ የሚቀበሉት ሱኒዎች ጠቅላይ ሚንስትርነቱን ይይዛሉ። በኢራን የሚደገፉት ሺያዎች ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት እና የፓርላማ አፈጉባኤነትን ይዞ..ቀሪ የምንስትርነት ቦታዎችንም በኮታ ተከፋፍሎ አገር ይመራሉ።
የሆነ ሆኖ የሀሰን ነስረላ መገደል በብዙ መከራ ውስጥ ላለችው ሊባኖስ ሌላ መከራን ልጨምር ይችላል። ዳግም የፖለቲካ ርዕደ መሬት የመከሰት ዕድል አለው። ይህ ከሆነ ከዚህ በፊት ያለፉበት አስቀያሚው የሀይማኖት የእርስበርስ ጦርነት ልለኮስ ይችላል። የአከባቢው አገራት ደግሞ እንደከዚህ ቀደሙ እጃቸውን እያስገቡ…ሳዉዲ ለሱኒ፣ ኢራን ለሺያ፣ እስራኤል ለክርስቲያኖቹ…ዱላ እያቀበሉ እሳቱ ላይ ነዳጅ በማርከፍከፍ እልቂቱን ሊያባብሱ ይችላሉ።
[ ኑሮን ለማሸነፍ ብሎ እየተቀጣጠለ ባለው የመከራ እሳት መሐል የሚገኙ እህቶቻችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን]
Via: ጥላዬ ያሚ

8 comments
እግዚአብሔር ሆይ ራራላቸው ለእህቶቼ
ጌታ ሆይ እጅህ ጠልቃ ይግባ 😭😭
“እስራኤል ለክርስቲያኖች” 🤡ሃሃሃሃ ንቃተ ህሊናህ ከዝንጀሮ ያነሰ ነው. የዚህ ፔጅ ባለቤት ድንቁርና ነው ጠላትህ አንብብ መሀይም.
ፈጣሪ ሊባኖስን ይጠብቅልን “ስለ ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን 🙏🙏🙏” …… ከሊባኖስ ከልጅሽ ጋር ነይ ….. መኃሊዬ መኃልይ
በሀገራችንም ሆነን በሰው ሀገር ተሰደንም ከጦርነት ሰቆቃ ነፃ መሆን አልቻልንም
ፈጣሪ በምህረት እጁ ይሸፍነን,🙏
ነብስ ይማር
Our ethiopia sister and brother 😭
Israel