🛑 “ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት በአራቱም ሃይማኖቶች”
የማርያምወርቅ የዘመኑ መንፈስ አስጨንቆታል አይቶ ሊያልፍ ሰምቶ ሊረሳው አልፈለገም፡፡ የመመረቂያ ርዕስ ሲመርጥ እንኳ በውስጡ ከሚብሰለሰለው ርዕሰ ጉዳይ እንዲወጣ የፈለገ አይመስልም ለዚህም ነው ጥንቅቅ አድርጎ ምርምሩን የሠራው፡፡
ኦርቶዶክስ ቤት ምን አሉ? ሙስሊሙስ ዘንድ? ካቶሊኩስ ስለዚህ ጉዳይ ምናለ? ፕሮቴስታቱስ? በማለት ለየትኛውም ወገንተኛ ሳይሆን ከብዙ ልፋትና መንከራተት በኋላ ይህን የመሰለ ድንቅ ስራውን አቅርቦልናል። ሥራው ምን ያህል ከባድ እንደነበረ ይህን መጽሐፍ የሚያነበው ይረዳዋል። በግምት እና በመሰለኝ ሳይሆን በሳይንሳዊ ዘዴ በስልት እና በስሌት የተሰራ ነው። ሀገሬን በአራቱ ሀይማኖቶች መነፅር ማየት እፈልጋለሁ። በተለይ ባለፉት 20 ዓመታት የሃይማኖቶቹ የጥበብ ሰዎች በመዝሙር፣ በመንዙማና በነሺዳ እንዴት እንዳገለገሉዋት ልወቅ ባይ ከእዚህ የተሻለ መጽሐፍ ሊያገኝ አያገኝም።
የማርያምወርቅ እጅግ ቅን ትሁት ፀሐፊ መሆኑን ስራውን በማየት መመስከር ይቻላል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት በአራቱም ሃይማኖቶች እንዴት ተገለፁ? ለምንድነው ዘማሪዎች እና ሙንሺዶቹ ትናንትን ናፍቀው ያ ቀን እንዲመለስ የሚጠይቁት? መጽሐፉን እያነበብን ከራሳችን ጋር ቆም ብለን እንድናወራ ይጋብዘናል።
…………..
መጽሐፉ የፊታችን እሁድ ጥቅምት 3 ቀን 2017ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት በግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል !
ሁላችሁም ተጓብዛችኋል!
ለሁሉም ሚዲያዎች ክፍት ነው!



