banner

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ለ7ኛ ጊዜ ወደ ኤርትራ አቀኑ

#FastMereja
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ በእ.አ.አ 2022 ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ለሰባተኛ ጊዜ ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

ሼክ ሞሃመድ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋራ ተገናኝተው የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት በሚጠናከርበት እንዲሁም በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ መንግስታዊ የሆነው የሶማሊ ብሔራዊ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ሃሰን ሼክ ሞሃመድ ባለፈው ሐምሌ ኤርትራን ጎብኝተው የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱም ሁለቱ መሪዎች “ታሪካዊ የሆነውን ግንኙነታቸውን በተመለከተ እንዲሁም በተለይም በፖለቲካዊ፣ የፀጥታ፣ በወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ መስኮች ግንኙነታቸውን በሚያሳድጉበትና የሁለቱን ሃገራት ሕዝቦች ጥቅም በሚያስጠብቁባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል” ሲሉ የኤርትራ ባለሥልታናት አስታውቀው ነበር።

10 comments

Markos Mathewos October 9, 2024 - 6:59 pm

ለምን 20 ግዜ አይሄድም።

Reply
Abdelaziz Seid October 9, 2024 - 7:00 pm

በቀጥታ አዋሩኝ ብሏቸዋል

Reply
ልጅ ሐብቴ ይዲድያ October 9, 2024 - 7:01 pm

ተባይ ነፍሳት ነገር ናቸው ተጨፍልቀው የእማማ ኢትዮጵያ አንድ ክልል አያሸንፉም!!!

Reply
Enelihun Dehna October 9, 2024 - 7:02 pm

የዛሬዉን አያደርገዉና የትግራይን ጦርነት ለመጀመር አብይ አህመድም በሳምንት ሦሥቴ ይመላለስበት ነበር ያዉ አብይ እንዳደረገዉ የሶማሊያዉ ሰዉዬም ጦርነት ለመጀመር ይሆናላ…😂😂😂😂😂

Reply
Wiz Abdu October 9, 2024 - 7:03 pm

የሁለቱም ሀገር አብዛኞቹ ዜጎች የሚኖሩት እኮ ኢትዮጵያ አዲስአበባ ነው🤗

Reply
Lataan Kan Addaamuuti October 9, 2024 - 7:03 pm

አንድ ላይ እንቀብራለን!👌

Reply
BEr Sguh October 9, 2024 - 7:06 pm

ለሚን ኤርትራ አይቀመጥም

Reply
Jemil Aman October 9, 2024 - 7:08 pm

ለምን ቀን ማታ አይመላለስም ሁለቱም በእጃችን ናቸው ማንሳት መጣል በኢትዩጽያ እጅ ነው

Reply
Tagel Tadele October 9, 2024 - 7:10 pm

ከገጠሙ መግጠም አንዴ ካየሮ አንዴ አስመራ ዘጠኝ ፈሳም ጎማ አይነፋም😍

Reply
Adugna Taffa October 9, 2024 - 7:18 pm

በየቀኑ መንገድ ከሚመላለሱ አንደኛውን የቤተመንግሥታቸውን መቀመጫ ኤርትራ ቢያደርጉ ይሻላል😂

Reply

Leave a Comment