#FastMereja l ተከሳሽ ሀብታሙ ዳምጠው ፋንታ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው በቦንጋ ከተማ ከአንዲት ግለሰብን የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት በመፈፀሙና ጥፋተኝነቱ በማስረጃ በመረጋገጡ ነው፡፡
በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ሀብታሙ ዳምጤው ፋንታ በቦንጋ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 በሚሆንበት ጊዜ የግል ተበዳይን ትከሻዋን በመንካት እና እጇን በመጨበጥ የ75 ሺህ ብር ሎተሪ ደርሶኝ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብሩን ለመቀበል መታወቂያ ስለሌለኝ ተባበሪኝ በማለት የማሳመኝ መንገዶችን በመጠቀም በምርመራው ስለማረጋገጡ ተገልፃል፡፡
የቦንጋ ከተማ ፖሊስ በምርመራው ግለሰቡ ከግል ተበዳይ ላይ ከባንክ አካዉንቷ 48 ሺህ ብር እንድታወጣ በማድረግ ብሩን፣የጆሮ ወርቅ እና የእጅ ስልኳን እንደወሰዱባት ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡ፖሊስ ግለሰቡን ከእነ እግዚቭቱ በመያዝ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በእግዝቭት ማስረጃ በማደራጀት ክስ እንዲመሰረትበት ለካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ህግ ልኳል፡፡
በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዬ ልዩ ወንጀሎች የዐቃቤ ህግ በክስ መዝገብ እንዳመለከተው ተከሳሹ የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀሙ ከፖሊስ ተጣርቶ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ መሰረት አድርጎ ዓቃቤ ህግ ግለሰቡን በወንጀል ህግ 692 ንዑስ አንቀፅ 1 ጠቅሶ በአታላይነት ወንጀል ክስ መስርቶበት ካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት አቅርቦታል፡፡
የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ግለሰቡ ላይ የመሰረተውን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ተከሳሹ በዐቃቤ ህግ የቀረበበትን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ የጠቀሰው ከፍተኛው ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግ ቅጣት ማክበጃና የተከሳሹን ቅጣት ማቅለያ ካደመጠ በኃላ የሁለቱንም ወገን መርምሮ ተከሳሹን የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ሀብታሙ ዳምጤው በሁለት አመት ከሶስት ወር እስራትና በአምስት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ሲወስንበት የግል ተበዳይ ንብረት እንዲመለስ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል፡፡

