📌 በስልጤ ሽማግሌ ትንቢት መሠረት ቀጣይ ብሩህ ጊዜ እንደሆነ ተተንብየዋል።
#FastMereja l በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ ሽልማት ቀበሌ ላይ ቀጨሞ ልማት ቡድን አንዲት የሀበሻ ላም ሶስት ጥጆችን ወለደች።
ማክሰኞ ጥቅምት 05/2017 ዓ ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ የወይዘሮ ሙርሺዳ ሽፋ የሀበሻ ላም ሶስት ጥጆችን በሰላም በመውለዷ ለአከባቢው ማህበረሰብ አግራሞትን ፈጥሮዋል።
ከዚህ ቀደም ይህቺው ላም በአንድ ወሊድ ጊዜ ሁለት ጥጃ መውለዷን ያስታወሱት ወ/ሮ ሙርሺዳ ሽፋ ሶስት ጥጃዎች መወለድ በእለቱ ድንጋጤ እንደፈጠረባቸው ሳይሸሽጉ ለአሊቾ ኮሚኒኬሽን ገልጸዋል።
ወንዱ ጥጃ ከተወለደ ጥቂት ሰአታት በኋላ የሞተ ሲሆን ሁለቱ ሴት ጥጆች በህይወት አሉ።
አቶ ሀይረዲን አለማር የአከባቢው ነዋሪና ታዋቂ ሽማግሌ ሲሆን ሁለት ጥጃ በአንዴ መወለድ አልፎ አልፎ ክስተት መሆኑን አንስተው ሶስት ጥጃ መወለድ በስልጤ ሽማግሌ ትንቢት መሠረት ቀጣይ ብሩህ ጊዜ እንደሚመጣ ተንብየዋል።
በአልቾ ውሪሮ ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ፅ/ቤት ባለሙያና አስተባባሪ ዶ/ር መሀመድ ከድር ክስተቱን በማስመልከት በሰጡት ሀሳብ እንደገለጹት በወረዳችን ከዚህ በፊት ያልተለመደ መሆኑን ገልጸዋል።
በወቅቱ ላሚቷ የአቅም ችግር ነበረባት በማለት የገለጹት ባለሞያው ሶስተኛው ጥጃም ሙሉ አካል ይዞ የተወለደ ቢሆንም በነበረበት ጫና በህይወት መቆየት እንዳልቻለ የገለጹ ሲሆን በአሁን ሰዓት ሁለቱ ጥጃዎችና ላሚቷ በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ብለዋል ሲል ፋስት መረጃ ከአሊቾ ውሪሮ ኮሚዩንኬሽን መረጃውን ተመልክቷል።

8 comments
በዚህ ኑሮ ውድነት
በተወደደ መኖ
ላሟ ኬኛ የሚል ቡድን ይመጣባችኋል ጠብቁ 🥴🥴
ተቃራኒ ነው እንዴ እሚያስቡ
የመሬት መንቀጥቀጡስ
እውነት ነው ብሩህ ጊዜ እንደሆነ ማሳያዎች አሉ
የታክሲ ታሪፍ በዶላር ሆኗል።
አንከባክቡት
Ewuyyy siyameru 😘
አንድ አይነት ጥጆች አለመሆናቸው
ባሏ ላይ መማገጧን አመላካች ነው