banner

በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ ሊዲያ ዓለም የተባለች ግለሰብ ሰርጓ በተፈጸመ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ እንደተገደለች ፖሊስ አ

በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ ሊዲያ ዓለም የተባለች ግለሰብ ሰርጓ በተፈጸመ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ እንደተገደለች ፖሊስ አስታወቀ።

#FastMereja I ሊዲያ ረቡዕ፣ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ አስር ሰዓት ላይ መገደሏን የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ሙሉ ብርሃን ካህሳይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው ባለቤቷ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ለፖሊስ እጁን እንደሰጠ እና በሕግ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ኮማንደሩ አክለዋል።

ተጠርጣሪው ብርሃነ ገብረጨርቆስ የተባለው ግለሰብ የአራት ቀናት ባለቤቱን አንቆ እንደገደላት የውቅሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ገብረ መድኅን ገብረጊዮርጊስ መናገራቸውን ድምጺ ወያነ ዘግቧል።

ግለሰቡ እጁን ለፖሊስ ከሰጠ በኋላ ራሱን ለማጥፋት የተለያዩ ሙከራዎች አድርጎ እንደበረ የገለጹት ኮማንደር ገብረ መድኅን ፖሊስ አስፈላጊውን ጥበቃ እና ክትትል እያደረገለት መሆኑን አክለው ተናግረዋል።

የውቅሮ ተወላጅ እና በአዲስ አበባ በንግድ ይተዳደር የነበረው ተጠርጣሪው ሙሽራ በውቅሮ ባረፈበት ሆቴል ውስጥ ንብረቱ እንደተገኘ ኮማንደሩ ገልጸዋል።

ተጠርጣሪው እና የተገደለችው ሊዲያ ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. በደማቅ የሰርግ ሥነ ሥርዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን መፈጸማቸው ተነግሯል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

10 comments

Mahder Setegn October 18, 2024 - 11:25 am

አረ ጭካኔ ቢቀርበትስ ባያገባት😭😭

Reply
So Lina October 18, 2024 - 11:29 am

የዘመኑ ወንዶች ግን ክፋታችሁ ወደር አጣ 😭

Reply
Hailay Hagos October 18, 2024 - 11:34 am

min gud new be fetari

Reply
Mulu Kefale October 18, 2024 - 11:34 am

በሬ ካራጁ ይውላል

Reply
Selina Demissie October 18, 2024 - 11:42 am

አምላክ ይጠብቀን እንጂ አስፈሪ ዘመን ላይ ነን

Reply
Aman Abyssinia-one October 18, 2024 - 11:43 am

ነፍስ ይማር

Reply
Kura Kura October 18, 2024 - 11:47 am

Rip😭

Reply
Mubi Lov You October 18, 2024 - 11:49 am

ደሞ አስፈላጊ ክትትልና ጥበቃ እየተደረገለት ነው ይላል እንዴ

Reply
Nake Gujo October 18, 2024 - 11:55 am

Rip😭😭😭

Reply
Senty Negn October 18, 2024 - 11:55 am

ምን ተፈጥሮ እደሆነ እነሱ እና ፈጣሪ ናቸው የሚያቁት መቸም ለመግዴል ብሎ አያገባትም🥺

Reply

Leave a Comment