0
ሙዝ ጭኖ ሲመለስ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ሰምጦ ከተሳፈሩ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ መገኘታቸውን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።
#FastMereja የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙት እና ገጽታ ግንባታ ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደገለጹት ትላንት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ የጀልባውን አሽከሪካሪ እና 15 የቀን ሠራተኞችን ከሙዝ ጋር ጭኖ ከአማሮ ዞን አቡሎ አልፋጮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባው መስጠሙን ተናግረዋል ።
በጀልባው ላይ ከነበሩ 16 ሰዎች ሁለቱ በጀርካን ላይ ተንሳፈው የተረፉ ሲሆን 14ቱ ባለመገኘታቸው ፖሊስ በፍለጋ ላይ መሆኑን ኮማንደር ረታ ተናግርዋል ።
15 ተሳፋሪዎች በሙሉ ሙዝ ለመጫን ከአርባምንጭ ዙሪያ አካባቢ የሄዱ መሆናቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።



7 comments
ምስክን ስያሳዝኑ😢
እግዚአብሔር ወቶ ከመቅረት አደጋ ይሰውረን🙏🙏🙏
Rip😭😭
💔ወይኔ ወገኔ 😭😭 ነፍስ ይማር 🙏
ነፍሰ ይማር
ያማል 🙏
እህ ሙዝ ብሎ 16ሰው አልገባኝም