#FastMereja I ከተመሠረተ አንድ ዓመት በላይ የሆነው ሆቶ ሬስቶራንት የሆስፒታሊቲ፣ የሆቴልና የሬስቶራንት ኢንደስትሪ በሚመለከት የሚያስፈልጉ ስልጠናዎች የታወቁ አሰልጣኞችን ወደ ሀገራችን በማስመጣት እንዲቻል ሌሎች ድርጅቶች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከብርትሽ በትለር ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ ተገልፆ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ሆቶ ሬስቱራንት ከብሪቲሽ በትለር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት እና የኢትዮጵያን የሆቴል ኢንዲስትሪ ለማዘመን የሚያስችል ውይይት ከተለያዩ የሆቴል እና የሬስቱራንት የስራ ኃላፊዎች ጋር በዛሬው ዕለት አትላስ አካባቢ በሚገኘው ሬስቶራንቱ ውይይት አካሂዷል።
የሆቶ ሬስቶራንት መስራች እና ኤክስኪዩቲቭ ሼፍ የሆኑት አቶ ዳንኤል ብርሀኑ እንደተናገሩት ከተጀመረ 18 ወር የሆነው ሆቶ ሬስቶራንት ከተለያዩ ኢንስቲትዩቶች ጋር በጋራ በመሆን የታወቁ ሼፎችን በማምጣት ኢንዱሰትሪው ምን እንደሚመስል ለተጠቃሚዎች እና ለእንግዶች ማሳየቱን ገልፀው በ18 ወር ውስጥ ከ60ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ማስተናገዳቸውን እና በዚህ አጭር ጊዜ ትልቅ ስኬት ሊመጣ የቻለው ሰራተኞቻችን ላይ ትልቅ ኢንቨስት ስላረግን ነው ብለዋል።
ሆቶ ሬስቱራንት ለ94 ሰዎች የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን የሆቴል እና መስተንግዶ ዘርፉ በሰው ሀይል በማሰልጠን በዘርፉ የሚስተዋለን ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ተቋማት ጋር እየሰራ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው በሆቴል ሙያ ስልጠና ረጅም አመት ልምድ ካለው ከብሪቲሽ በትለር ኢንስቲትዩት ጋር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።




