#FastMereja I A Plus Trading በቦሌ ሳውዝ ጌት ኘላዛ የሴቶች ፋሽን አልባሳት መሸጫ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ።
በወንዶች ፋሽን ኢንዱስትሪ የ4 አመታት ልምድ ያለው ኤ ፕላስ ትሬዲንግ በከተማ ውስጥ በሚዘጋጁ የተለያዩ መርሐግብሮች ላይ የሚለበሱ የሴቶች እና የወንዶች አልባሳትን ከውጭ ሀገር በማስመጣት በሽያጭ ላይ እንደሚገኝ የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሕይወት መቆያ የፋሽን ሱቁ ተመርቆ በተከፈተበት መርሐግብር ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
ከአውሮፖ፣ ከኤዥያ እና ከአሜሪካ ሀገራት ዘመኑን የተከተሉ የወንዶች እና የሴቶችን አልባሳት እና ጫማዎችን በብዛት እንዲሁም ለሁሉም የእድሜ ክልል በሚስማማ መንገድ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ኤ ኘላስ ትሬዲንግ በቅርቡ ሶስተኛውን የመሸጫ ሱቅ እና በቀጣይ ኤ ኘላስ የህጻናት አልባሳት መሸጫ ሱቅ ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ወይዘሮ ሕይወት መቆያ ገልጸዋል።
ድርጅቱ ለበርካታ ዜጎች ቋሚ እና ጊዚያዊ የስራ እድል በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የፈጠረ ሲሆን ድርጅቱ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በወይዘሮ ሄለን የተመሠረተው ግሎሪ ፋውንዴሽን በጋራ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።





10 comments
እስቲ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ አታስነሱብን
በሉ ወደ ስምጥ ሸለቆ ላኩልን በነሱ ምክንያት በመሬት መንቀጥቀጥ ለሁለት መከፈል አንፈልግም 😳 ራሳቸውን ይደበላልቃቸው ከመአቱ!
ስኬት ለአንድ አትሌት የኦሎምፒክ ውድድርን ማሸነፍ እና ወርቅ ማግኘት ሊሆን ይችላል፣ ለአንድ ተዋናይ እንደ ኦስካር እና ግራሚ ያሉ ሽልማቶችን ማሸነፍ ሊሆን ይችላል፣ ለአንድ የንግድ ድርጅት ባለቤት ደግሞ በአለም ላይ ካሉ ስኬታማ 500 ድርጅቶች ቀዳሚው ድርጅት መሆን ሊሆን ይችላል የሴት ስኬት ወንድ ያስብላል በርቺ ጀግኒት🥰
#አፍራሽ ብዬ ነው ያነበብኩት 😂🙌
ከንቲባዋ መመረቅ ነበረበወት አንደኛው የቦሌ የኮሪደር ልማት ነው
Wow what a wonderful news !!! It will be a backbone for our economy, which can help our 120 million poor ppl!
አሁን ለዚህ ዜና ትሰራላቹ ይገርማል
ደሞ ሊያሻፍዱን ነዋ
Congratulations yene Gobez am so proud of you 👏
Congratulations hiwiyee