banner

ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባት ሴት ገንዘብ መሰብሰብ አግባብ አይደለም ተባለ።

#FastMereja I ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በሴቶች ህፃናት ላይ የሚሰራ በተለይ የስንቅ በጎ አድራጎት መስራት እና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሐያት መሀመድ በበርካታ መከራ ውስጥ ያለፈች፣ አስገድዶ መደፈር የገጠማት፤ በስደት ከ16 ዓመት በላይ በጀርመን የኖረች ስትሆን የህፃናት እና ሴቶች ጸታዊ ጥቃት ይቁም፣ ስደት ይብቃ በማለት የወገኖቿን ጥሪ ድምፅ በመስማት ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር በማቋቋም በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በዱባይ እና በመካከለኛው ምስራቅ ደጋግ ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።

ከተመሰረተ አራት አመት ያስቆጠረው ስንቅ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሐያት መሀመድ ከ16 ዓመት በኋላ ወደ ሀገሯ መጥታ ዛሬ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙኋን መግለጫ ሰጥታለች።

ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባት ሴት ገንዘብ መሰብሰብ አግባብ አይደለም ያለችው ወ/ሮ ሐያት ቅድሚያ ተጎጂዎች የስነ ልቦና እና ህክምና ነው ማግኘት ያለባቸው ብዬ አመናለው ቀድሞ ገንዘብ መሰብሰቡ አግባብ አይደለም ብላለች።

ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ከ8 ሰአት ጀምሮ በህፃናት ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ መድረክ እና የስንቅ በጎ አድራጎት ተቋም የቦርድ ስብሰባ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።





6 comments

Strong Voice October 19, 2024 - 5:25 pm

በደቡብ ኢትዮጵያ ዎላይታ ዞን የሰሩበትን ደመወዝ የጠየቁ መምህራን መታሰራቸው ተሰማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን በዳሞት ወይዴ ወረዳ ሶስት መምህራን የሐምሌ ወር ደሞዛቸውን ስለጠየቁ ብቻ ትላንት ሐሙስ 7/2/2017 ከሌሉት 9:00 አካባቢ ከቤታቸው በፀጥታ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ቤተሰቦቻቸው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

እንደ ቤተሰቦቻቸው ገለፃ በፀጥታ ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት መምህራን በአከባቢያቸው ባለው ፓሊስ ጣቢያ ሳይሆን ዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ሰሊሆም ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ አስረድተዋል።

እነኚህ የሰሩበትን ደመወዝ የጠየቁ መምህራን፦ መ/ር ወንድምዓለም ሙላቱ፣ መ/ር ዳንኤል ፋልታሞ እና መ/ር መስፍን ዳዊት ስለመሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባገኘው መረጃ መሰረት፦ በዞኑ የከተማና ወረዳ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ትግቢውን አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የተረጋገጠ ሲሆን በዚህም ምክንያት በተለይም በግል የጤና ተቋማት ለመታከም ዐቅም የሌላቸውና ከዚህ በፊት በማኅበረሰብ ጤና መድኅን ሽፋን በነዚህ ተቋማት አገልግሎት ሲያገኙ የቆዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በከፋ የጤና ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

በዞኑ በሚገኙ ወረዳ ውስጥ ለመምህራኑ ተገቢው ደመወዝ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከሚያዚያ ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ከ65 በመቶ በላይ መማር ማስተማር ስራ ተቋርጧል፡፡

የመንግስት ሰራተኛ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት ተነፍጎ በዞን ውስጥ የሚሠሩ ብዙ ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች በተቆራረጠ ክፍያ እና ደመወዝ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምክንያት ለከፋ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች ተጋልጠዋል።

ሠራተኞቹ ሌላ ገቢ እንደሌላቸውና ደመወዝ በመቋረጡ ምክንያት ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው የዕለት ጉርስ ለማግኘት እንደተቸገሩ፣ የቤት ኪራይ መክፈል እንዳልቻሉ፣ ከደመወዝ ጋር በተያያዘ በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት ብድርም ማግኘት ስላልቻሉ ሕይወታቸውን ለማቆየት የቤት እቃ በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

አሁን አሁን በአከባቢው ደመወዝ መጠየቅ ወንጀል እስኪመስል ድረስ ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ የደመወዝ ክፍያ በፈለገበት ሰዓት ቆራርጦ መክፈል የተለመደ እና ህጋዊ አሰራር ከሆነ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡

ከዚህም የተነሳ የሰራተኛው ህይወት ከድጡ ወደማጡ እንዲገባ በመዳረጉ አቤቱታቸውን እንኳን የሚሰማ ጠፍቶ ችግሮች እየተባባሱ ከዕለት ወደዕለት ወደ ባሰ ድህነት ውስጥ ሰራተኛው እንዲገባ ተዳርጓል፡፡

ከሁሉም በላይ ከደመወዝ አለመከፈል ጋር ተያይዞ ቅሬታ እና ተቃውሞ ባሰሙ፤ ፍትህ በጠየቁ ግለሰቦች ላይ ማስፈራራት፣ ዛቻ፣ ጭምር እየደረሰባቸው የሚገኝ ስለሆነ የፌዴራል የመንግሥት፤ የክልል የመንግሥት እና የዞን የመንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እርምጃዎችን በመውሰድ ለሠራተኞች ደመወዝ ወቅቱን ጠብቆ መከፈሉን እና ሰብአዊ መብቶቹ መከበራቸውንና መጠበቃቸውን እነዲያረጋግጡ ጥሪ ቀርቧል።

የሥራ መብት በተለያዩ ዓለምአቀፍና አህጉርአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ዕውቅና ካገኙ መሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች አንዱ ሲሆን የሥራ መብት የሠራተኞች ደመወዛቸውን በሙሉና በወቅቱ የማግኘት መብትንም የሚጨምር ሲሆን ለሠራተኞች ተገቢውን ደመወዝ እና ሌሎች ክፍያዎችን በወቅቱ አለመክፈል ሠራተኞች እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር የሚችሉበትን መንገድ የሚገድብ እና የሥራ መብት ጥሰት ሆኖ የሚቆጠር ነው ይላል፡፡

የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት በደመወዝ ጥበቃ ስምምነት 1949 (ቁጥር 95) አንቀጽ 12 እና በደመወዝ ጥበቃ ምክረ ሐሳብ 1949

👊👊👊👊👊

Reply
Yetnayet Endale October 19, 2024 - 5:32 pm

የህሊና ስብራት በገንዘብ ሃይል አይመለስም ልክ ናት!!!!!

Reply
Cent Solo October 19, 2024 - 6:18 pm

ከፈረሱ ጋሪው እንዳይቀድም ልክ ነች 🙏

Reply
Mesi Mesi October 19, 2024 - 7:01 pm

አያት ጀግናዋ እንኳን በሰላም መጣሽ

Reply
Yeglie Amare October 19, 2024 - 7:12 pm

በርች ሰዉ ህልሙን ሲኖር ያስደስታል አላህ ያግዝሽ 😇❤️🙏🏻

Reply
Wosen Kibie October 19, 2024 - 7:44 pm

ለዳይሬክተር ስንታየሁስ

Reply

Leave a Comment