banner

ሰላሳ ሚሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት በነፃ ለመስጠት የማያስችል ንቅናቄ ተጀመረ

#FastMereja I ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ብቁ ንቁ ዜጋ ጀግና ዜጋ ለማፍራት የንቅናቄ መክፈቻ ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከመንግስት ባለድርሻ አካላት እና ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በወዳጅነት ፓርክ የመክፈቻ መርሀ ግብር አካሄዱ፡፡

ይህ ንቅናቄ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች ሰላሳ ሚሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት በነፃ ለከተማችን ነዋሪዎች ደግሞ ለአንድሺ ሰዎች ለመስጠት በማቀድ በዛሬ ዕለት መርሀግብሩን መጀመራቸውን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

ተቋማቱ የሦስትዮሽ ስምምነት በማድረግ 90 ቀናት ሁለንተናዊ ለውጥ ማዕከል ጀግና ዜጋ የማፍራት ንቅናቄ በውፍረት እና ከውፍረት ጋር የሚመጡ ተያያዥ በሽታዎች የተጠቁ ዜጎችን እንዲሁም በተለያዩ ሱሶች የተያዙ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ሥልጠና የአካል ብቃትና ሥርዓተምግብ ስልጠና በነፃ በመስጠት በአካል በመንፈስ በስነልቦና ብቁ እንዲሁም ባለራዕይ ጀግና ዜጋ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ይህን ስልጠና በስፋት ለመስጠት የታሰበው ብዙዎችን ከህመም ከሱስ ተስፋ ከመቁረጥ ተመልሰው ብርቱ ንቁ ጀግና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው።





1 comment

ጤናሁን ተስፋዬ October 20, 2024 - 10:28 am

የማያስችል ?

Reply

Leave a Comment