#FastMereja I የጊዜያዊ ዕውቅና ለማግኘት ሲከፍሉ የነበረውን 100 ብር ወደ 15ሺ ከፍ ተደረገ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጊዜያዊና ሙሉ ዕውቅና ለማግኘት የሚጠበቅባቸው ክፍያ መሻሻሉን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፤ ለጊዜያዊ ዕውቅና 15ሺ፣ ለሙሉ ዕውቅና 30ሺ ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን ባወጣው መግለጫ ለሀገር አቀፍ እና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፍኬት ለማግኘት 100 ብር ብቻ ያስከፍል እንደነበር አውስቶ ከጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በኋላ ግን ክፍያው 15ሺ ብር መሆኑን እወቁልኝ ብሏል።
በተመሳሳይ የሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ ዕውቅና ለማግኘት እስከ ትላንት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ይከፍሉ የነበረው 200 ብር ብቻ መሆኑን አስታውሶ ከዚህ በኋላ ግን ክፍያው 30ሺ ብር ነው ሲል አስታውቋል።
የተመዘገቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር የአገልግሎት ክፍያ ሲያስከፍል እንደነበር ጠቁሞ ከዚህ በኋላ ግን ሰነዶቹን ያሻሻለ ፓርቲ 5ሺ እንዲከፍል ወስኛለሁ ሲል ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ ክፍያውን ያሻሻልኩት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ እና የሰነድ ማሻሻያ አገልግሎት ክፍያ መጠኑ በቦርዱ እንዲወስን በአዋጅ ስልጣን ስለተሰጠኝ ነው ብሏል።
ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው።

5 comments
Pp yikflale
ምን ይጠቅማል ፓርቲ እስከዛሬ ድረስ መመዝገቢያ 200 እና 100 ብር መሆኑ ራሱ የሚደንቅ ነው።
የቀበሌ መታወቂያ ራሱ ተወዷል
እንደውም 1,000,000 በላይ መሆን ነው ያለበት። ከሚያነፍሩን በፓርቲ ብዛት ህዝብ መቀለጃ ከሚሆን።
አታካብዱ ብዙ የሚያሳስበን ጉዳይ አለ ጎበዝ
because it is difficult to import political party. Dollar🔝
100ወደ 15000ከባድ ነው
አሁን የኢትዮጱያን ህዝብ የሚያሳስበው በልቶ የመኖር ጉዳይ ነው