banner

ከ8ኛ ክፍል እስከ ማስተርስ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

#FastMereja I በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ዝግታ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ አንድ ግለሰብ ልዩ ልዩ ማህተሞችና ቲተሮችን በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደሚያዘጋጅ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በጥናት ላይ የተመሠረተ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ከሰራ በኃላ የተገኘ ውጤት መሆኑን ከፖሊስ መምሪያው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፖሊስ ተገቢውን የህግ ስርዓት ተከትሎ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ በርካታ የተዘጋጁ እና ሊዘጋጁ የተሰናዱ ሀሰተኛ ሰነዶችን እንዲሁም ግለሰቡ ሀሰተኛ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችም ተይዘዋል፡፡

ተጠርጣሪው ሀሰተኛ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸው የመንግስትና የግል ተቋማት 51 ክብ ፣ 73 የግርጌ ማህተሞች፣ አምስት ፕሪንተሮች ፣ አንድ ኮምፒተር፣ አንድ ላፕቶፕ እንዲሁም በሃሰተኛ መንገድ የተዘጋጁ የ8ኛ ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል እንዲሁም የዲፕሎማ፣ የዲግሪ፣ የማስተርስ የትምህርት ማስረጃዎችን በተጨማሪነት መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ በሀሰተኛ ሰነድ አማካኝነት የሚፈፀሙ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመከላከል ህገ-ወጦችን ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባና ተቋማት ለተለያዩ ጉዳዬች የሚቀርቡላቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት ሊያረጋግጡ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡





6 comments

Tinsu Tinsina October 24, 2024 - 2:55 pm

የአቢቹ አይጠፋም እዚ ዉስጥ

Reply
ሙሪድ ኢጄንሲ October 24, 2024 - 2:56 pm

የአብይ አህመድ እና የዳኤል ክብረት አይጠፋም

Reply
Mekedes Mekdi October 24, 2024 - 2:57 pm

ወረቀቶቹ ውስጥእንደኔ የጠቅላያችንን ስም የፈለገ አለ? 😁😁

Reply
Samson Getahun October 24, 2024 - 2:58 pm

በየወረዳው መረጃን ስካን የሚያደርግ ማሽን ያስፈልጋል ቀጣሪ መረጃን ለማጣራት ወረዳ ሄዶ በጥቂት ብር ክፍያ እርግጠኝነቱ ቢረጋገጥ ቀጣሪና እንደዚህ አይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን በቀላሉ መያዝ ይቻላል

Reply
Eli Jah October 24, 2024 - 2:59 pm

ሰርቶ መብላት የማይቻልበት ለሰው መስራት የማያስከብርበት ሀገር¡😞

Reply
ገብርዬ ጌጤ ካሳውደግ October 24, 2024 - 2:59 pm

ይሄ ግለሰብ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ይሁንልን!!!

Reply

Leave a Comment