banner

በአንድ ቢሊዮን ብር ሆስፒታል ሊገነባ እንደሆነ ተገለፀ

በአንድ ቢሊየን ብር ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚያገግሙበት ሆስፒታል ሊገነባ እንደሆነ ተገለፀ።

ስንቅ በጎ አድራጎት ድርጅት እና የሴቶችና ልጃገረዶች ድጋፍ ኢትዮጵያ በህፃናት ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

“የሕፃናት እና ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ይቁም ስደት ይብቃ!” በሚል መሪ ሀሳብ የተመሠረተው ስንቅ በጎ አድራጎት ድርጅት ባለፉት አራት አመታት ውስጥ የሰራቸውን ተግባራት ሪፖርት አቅርቧል።

በመርሐግብሩ ላይ የስንቅ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሐያት መሀመድ እንደገለጹት በህጻናትና ሴቶች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከልና ለማስቆም የሁሉም ዜጋ አስተሳሰብ መዳበር አለበት ያሉ ሲሆን በተለይም በአካል ጉዳተኛ ሴቶችና ህጻናት ላይ በርካታ ጥቃት እየተፈጸመ እንደሆነና፤ ጥቃቱም የሚፈጸመው በቅርብ የቤተሰብ አባል መሆኑን ተከትሎ ህብረተሰቡ እንዳይማርበትና ጥንቃቄ እንዳይደረግ አድርጎታል ያሉ ሲሆን ሁላችንም በጋራ በመሆን የችግሩን አሳሳቢነት መቀነስ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ስንቅ የበጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ቢሊየን ብር ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች የሚታከሙበት ሆስፒታል ለማስገንባት እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ወ/ሮ ሐያት መሀመድ በንቅናቄው መርሐግብር ላይ ተናግረዋል።

ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በሴቶች ህፃናት ላይ የሚሰራ በተለይ የስንቅ በጎ አድራጎት መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሐያት መሀመድ በበርካታ መከራ ውስጥ ያለፈች፣ አስገድዶ መደፈር የገጠማት፤ በስደት ከ16 ዓመት በላይ በጀርመን የኖረች ስትሆን የህፃናት እና ሴቶች ጸታዊ ጥቃት ይቁም፣ ስደት ይብቃ በማለት የወገኖቿን ጥሪ ድምፅ በመስማት ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር በማቋቋም በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በዱባይ እና በመካከለኛው ምስራቅ ደጋግ ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።





3 comments

Mohammed Salih Muhie October 24, 2024 - 4:25 pm

ጸታዊ ጥቃቱን ከምንጩ ማድረቅ ይሻላል // ይህ እኮ ይደፈሩ ; ይጠቁ ይታከማሉ እንደማለት ነው ግን የሥነ ልቦና ስብራት መጠገን ይከብዳል

Reply
Olbaanaa Tulluu October 24, 2024 - 4:28 pm

1ቢልዮን ከምያወጡ ጥቃት አድራሺው መ*ግደል ይሻላል ። ይሄ ማበረታቻ ይመስለኛል ።

Reply
Teddy Demeke October 24, 2024 - 4:30 pm

ጥቃት አድራሾች ላይ ህጉ ተሻሽሎ የሞት ፍርድ ቢኖር

Reply

Leave a Comment