banner

ቶታል ኢነርጂስ የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ አሸናፊዎችን አሳውቋል።

#FastMereja I ቶታል ኢነርጂስ በአራተኛ ዙር ውድድር የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ አሸናፊዎችን አሳውቋል። የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ ውድድርን ካሸነፉት ውስጥ:-

📌 መንበሩ ዘለቀ በኢኖቭ አፕ ምድብ ውስጥ ሶላር መቀስ የተባለ መሳሪያ በመስራት ፣
📌 ኤርሚያስ ተፈራ በሳይክል አፕ ምድብ ውስጥ ኤኮ ፓኬጅ እና ቦርሳ በመስራት
📌 አዱኛ ንጋቱ በፓወር አፕ ምድብ ምርጡ ዘላቂ እና ተመጣጣኝ የባዮ ጄል ነዳጅ በማምረት ተሸላሚ መሆን ችለዋል።

ፕሮጀክታቸውን ለማልማት ይችሉ ዘንድ የስራ ፈጣሪዎቹ ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን በቢዲ ኮንሰልት አማካኝነት ፕሮጀክታቸውን እንዲያለሙ የግል ድጋፍ እንዲሁም አላማቸውን በተመለከተ ግንዛቤ ለማዳበር መንገድ ይመቻችላቸዋል ተብሏል።

ለውድድሩ 719 ሰዎች የተመዘገቡ እንዲሁም ከነዚህ ውስጥ የተሟላ ማመልከቻ ያቀረቡት 207 ሲሆኑ ፕሮጀክታቸውን ለሀገር ውስጥ ዳኞች ያቀረቡት 14 የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።



Leave a Comment