#FastMereja I አላሚ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት በአዲስ አሰራር እና ቴክኖሎጂ ታግዞ በአዲስ አበባና በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ተደራሽ ለመሆን አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ ለበርካታ ወገኖች የስራ ዕድል የፈጠረው አላሚ ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ የፈጣን መልዕክን በጥራትና በታማኝነት እንዲሁም በፍጥነት አገልግሎት ለመስጠት ስራውን ጀምሯል::
አላሚ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ሁሉንም የሀገራችን ክፍሎች ሊሸፍን በሚችል የሎጅስቲክስ አገልግሎት የተደራጀ ሲሆን የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አቅም አለው:: አገልግሎቱም በአዲስ አበባና በሀገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል ።
ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች የቤት ለቤት አገልግሎት፤ ክፍያን መቀበል፤ የመጋዘን አገልግሎት፤ ክልላዊና ሀገራዊ መልዕክት አገልግሎት ፤ የተመለሱ እና የተቀየሩ ዕቃዎችን ወይም መልዕክቶችን ማስተዳደር ይገኙበታል ።
አላሚ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት በመላው ሀገራችን ለስራ ያዘጋጀው መጋዘኖች ፤ ተሽከርካሪዎች፤ ሞተር ሳይክሎችና ብስክሌቶች ያሉት ሲሆን ለባለ ንብረቶች የስራ ዕድል ለመፍጠርም የብስክሌት፤ ሞተር ብስክሌት፤ ጭነት መኪኖች መጋዘንና የሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል ወደፊትም ይፈራረማል፤ በዛሬው ዕለትም ከጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ለመስራት ተፈራርሟል::
አላሚ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ታማኝ ቀልጣፋ በትክክለኛው ሰዓት እና ቦታ የተሰጠውን ንበረት በእምነት የሚያደርስ እንዲሁም ደንበኞችን ማዕከል ያደረገና ለተጠቃሚዎች መፍትሄ ይዞ የመጣ ነው:: በአጭር የመልዕክት ቁጥር 9959 ላይ በመደወል አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል::




