#FastMereja I ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም በፒኮክ ፓርክ ተማሪዎቹን አስመረቀ። ተመራቂ ተማሪዎች በሜካፕ፣ በጥፍር፣ በአይላሽ እና በፀጉር ሞያ የሰለጠኑ እንደሆነ ተነግሯል።
የቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቃልኪዳን ፍርዱ ባደረገችው ንግግር በተቋሟችን ተምረው የወጡ በርካታ ተማሪዎች በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የራሳቸውን የውበት ሳሎን ከፍተው በስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ በተጨማሪም በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በዱባይ፣ በእስራኤል እና በጀርመን ሀገራት በሚገኙ ትላልቅ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጻለች።
ከፍለው መማር ለማይችሉ ዜጎች ነፃ የትምህርት እድል በመስጠት ተቋሙ በርካታ ዜጎችን የውበት ሞያ ባለቤት ማድረጉ ተነግሯል።
ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ከተመሰረተ በ3 አመታት ውስጥ ከ1ሺ በላይ ዜጎች አሰልጥኖ የሞያ ባለቤት ማድረግ ችሏል። በቀጣይ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልል ከተሞች ለመክፈት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
#kal_makeup_school
#makeup_by_kal
#arts_tv
#topazion_pictures
#focus_studio
#family_design





3 comments
ወይ ያየ ዘልደታ ደግሞ ሜካፖ ስር ምን ያርመጠምጥሀል🤭
አይ እገሌ
Yaya ነው🙄