ከኢትዮጵያ ሕዝብ 76% ኔትወርክ ባለበት አካባቢ ቢኖርም አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት እንደማይጠቀም የግሎባል ሲስተም ፎር ሞባይል ኮምዩንኬሽንስ ማኅበር ጥናት ይፋ አደረገ።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ክፈቱትን ለመቀነስ መሠረተ-ልማት ማስፋፋትን ጨምሮ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።
በኢንተርኔት አገልግሎት ሽፋን ውስጥ ከሚገኙት የቴሌኮም ተጠቃሚዎች መካከል 24% የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ብቻ የኔት ዎርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው ተባለ።
ከኢትዮጵያ ህዝብ 76% የሚሆነው ምንም እንኳን ኢንተርኔት አገልግሎት ያለበት አካባቢ ቢኖርም አሁንም በኔትዎርክ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት እንደማይጠቀም ግሎባል ሲስተም ፎር ሞባይል ኮምንኬሽን አሶሲየሽን (GSMA) ባወጣው ሪፓርት ገልጿል
ጂ.ኤስ.ኤም ኤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሪፖርት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ከ 4 አመት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2028 ኢትዮጵያ ከሚኖራት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ አስተዋጽዖ ያደርጋል ብሏል።
አሁን እስካለንበት የፈረንጆቹ 2024 ድረስ ከ90 ሚሊዮን በላይ የተንቀሳቃሽ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች በሀገሪቱ እንዳሉ የተነገር ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ የአጠቃቀም ክፍተት እንዳለ የጠቆመው ሪፓርት ምንም እንኩዋን ፣ በኔትወርክ ሽፋን ቢኖርም 76 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት እይጠቀምም ሲል ሪፖርቱ አትቷዋል ፡፡
DW ያነጋገራቸው አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሞባይል ስልክ ቢኖረኝ እጅ ስልኬ የኢንተርኔት ተጥዕቃሚ አይደለሁም ሲሉ ይናገራሉ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራስኪያጅ ፍሪህይወት ታምሩ ባለፉት ጥቂት አመታት ያሳየነው የ መሰረተ ልማት እድገት እና ፈጣን እንቅስቃሴ ይህንንኑ ክፍተት ለመሙላት ነው ሲሉ በያመቱ የተጠቃሚው ቁጥር መጨመር ምስክር ነው ብለዋል
በኢትዮጵያ ሁሉም የመንግስት አገልግሎት ክፍያዎች በሙሉ በቴሌብር ብቻ እንዲሆኑ መደረጉ ይታወቃል።
ዘገባው የDW ነው።

10 comments
አሁን ገና ገባኝ ጭማሪው የመጣብን የነሱን እየከፈልን ነው ማለት ነው”
እኔም ተጠቅሜ አላቅም፡፡
ኦ ድረድግ አለ ጉራጌ
ዋጋው ውድ ሰለሆነ ይሆናል
እኔ አንዱ ነኝ
ችግሩ ዳቦ እንጂ እንተርኔት አይደለም
24% እየተጠቀምን ነው ያግማማነው በስማም ቱ
ተገላገሉ አ
Yetetekm rasu min ateref were bicha
24% ብቻ ተጠቅመን ነው ኔቴወርኩ የሚዘገየው 50% ተጠቃሚ ብንሆን ምን ሊውጠን ነው