banner

የጋሽ ማሕሙድ አሕመድ የመድረክ ስንብት

#FastMereja I በአገራችን ዘመናዊ ሙዚቃን ከባህላዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ጋር አዋህዶ በመዝፈን በአገራችን ቀደምት የሙዚቃ ንጉስ የሆነዉ አርቲስት የክብር ዶክትር ማሕሙድ አሕመድ ክብር ይገባዋል በማለት አድናቂዎቹ እና ወዳጆቹ በመሰባሰብ ኮሚቴ በማዋቀር ላለፉት ሁለት አመታት የተለያዩ ስራዋችን ሲሰሩ እንደቆዩ ዛሬ አርብ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ኮሜቴው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ኮሚቴው እየሰራ ካላቸው መካከል የጋሽ ማህሙድን የመጨረሻ የሙዚቃ መድረክ ማዘጋጀት፣ የጋሽ ማህሙድ የህይወት ታሪክ መጽሃፍ ህትመትና ምረቃ፣ በጋሽ ማህሙድ ስም መንገድ / አደባባይ ማሰየም፣ የጋሽ ማህሙድን ሃውልት ማቆም ይገኙበታል።

የጋሽ ማሕሙድን የመጨረሻ የስንብት የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ከጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር ኮሚቴው የውል ስምምነት ገብቶ ሙሉ ሃላፊነት ተቀበሎ ይህንን የመጨረሻ የሙዚቃ መድረክ ለማዘጋጀት ተስማምተናል ብለዋል።

ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በሚደረገው ኮንሰርት እስከ 25,000 ታዳሚያን ይገኛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

ጋሽ ማሕሙድ በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፥ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያበረከተው አስተዋጽኦ ለአሁኑ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሆነ የሙዚቃ ንጉስ ነው::





Leave a Comment