
ጥቅምት 24 ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ ታላቅ የበረከትትና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል
ጎጃም ባርዳር ዙሪያ የሚገኘውና ከ400 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ፃዲቁ አባት አቡነ ሐራ ድንግል ከፈጣሪያቸው በተገባላቸው ቃል በመቃብራቸው አፈር እምነትና በጠበላቸው እውራንን እያበሩ በደዌ የተመቱትን እየፈወሱ ገቢረ ተዓምራቸውን የሚያሳዩበት ጥንታዊ ገዳም ነው።
ፈውስና ምህረት ፈላጊው ከፃዲቁ ላለመራቅ በገዳሙ እርስት ላይ ቤት አሰየሰራ ኑሮውን መሰረተ። ገዳሙ ተጣበበ
እድሜ ጠገብ የገዳሙ መነኮሳት በወዳደቀ ጎጆ ውስጥ በችግር ላይ ይገኛሉ። በገዳሙ ዙሪያ በተስፋፋው መንደር ለገዳሙ ቅድስና የማይመጥኑ ተግባራት ይፈፀማሉ።ፈውስ ፍለጋ ከመላው አገሪቱ የሚጎርፈው ምዕመን በየቁጥቋጦው ስር እያደረ ጠበል ይጠመቃል እምነት ይቀባል። ይህን ችግር ለመቅረፍና የገዳሙን እርስት ለማስመለስ ብሎም መልሶ ለማልማት ከፍተኛ ወጪ በመጠየቁ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማዘጋጀት ግድ ሆኗል። በመሆኑም የዚህ የበረከት ጉባኤ ጥቅምት 24 በማሊኒየም አዳራሽ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ ይካሄዳል
ትኬቶችም አየየተሸጡ ነው።
በመላው ዓለምና በኢትዮጵያ የምትገኙ የፃዲቁ ወዳጆች የዚህ በረከት ተካፋይ እንድትሆኑ በፃዲቁ ስም ተጋብዛችሗል
ትኬቶቹ:-
በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት
-ሰንበት ት/ቤቶችና ወጣቶች ማህበር
-በአሃዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
_በአባይ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
-በማህበረ ቅዱሳን ሁሉም ሱቆች
-6 ኪሎ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በሚገኘው የገዳሙ ሱቅ
-ልሄም በርገር ቤት ሜክሲኮ ይገኛሉ
ኑ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ
የፃዲቁን ቤተ ፈውስ ያስከብሩ
በእንተ አቡነ ሃራ ድንግል
ለበለጠ መረጃ
251918406967
0911636818
CBE 1000610362463
0