0
#FastMereja I ላየን ኢትዮጵያ ሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ ኮሌጅ በሆቴል፣ በቱሪዝምና ቢዝነስ የትምህርት ምስኮች ያሰለጠናቸውን 450 ተማሪዎችን ዛሬ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በብሔራዊ ቴአትር አስመርቋል።
ላየን ኢትዮጵያ የሆቴል፣ የቱሪዝምና የቢዝነስ ኮሌጅ ከተመሠረተ 20 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ባለፉት አመታት 15ሺህ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል። ከፍለው መማር ለማይችሉም ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት እንዲማሩ ተደርጓል።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ስለሺ ግርማ እና የኮሌጁ ባለቤት አቶ ሙሃመድ አወል ለተመራቂ ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፏል።




