banner

የትጥቅ ግጭት ባለበት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ መምህራን በደሞዝ መስተጓጉል እና መዘግየት “ከባድ ችግር”

የትጥቅ ግጭት ባለበት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ መምህራን በደሞዝ መስተጓጉል እና መዘግየት “ከባድ ችግር” ውስጥ ነን ይላሉ።

መምህራኑ የጥቅምት ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸውም ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመትም ለሦስት ተከታታይ ወራት ደሞዝ ሳይከፈላቸው መቆየቱን የተናገሩት መምህራን ደሞዝ አለመከፈሉ ይቀጥላል በሚል ችግር እና ስጋት ውስጥ ናቸው።

“ንብረታችንን እየሸጥን ነው” ያሉ አንድ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መምህር ሁኔታውን “ፈታኝ” ብለውታል።

“ያለንን ንብረታችንን ሸጠናል። አልጋ ሸጠናል፤ ወንበር ሸጠናል፤ ቴሌቪዥን ሸጠናል። ጓደኞቼ የትዳር ቀለበታቸውን እስከ መሸጥ ደርሰዋል። . . . በዚያ ላይ ኑሮ ውድነቱ አለ። አንድ ኩንታል ጤፍ 11 ሺህ ብር ገብቷል። በቆሎ አራት ሺህ፤ አምስት ሺህ ነው የሚሸጠው” ይላሉ የሁለት ልጆች አባት የሆኑት መምህር።

“ያለው አማራጭ ወደ ተለያየ ቦታ መሰደድ ነው” ያሉ ሌላ መምህር፣ ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር መምህራን የቤት እቃቸውን እየሸጡ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

“አልጋውን የሸጠ መምህር አውቃለሁ። . . . ” በማለት መምህራኑ ለልጆቻቸው ዳቦ ለማቅረብ ሲሉ ዋጋ የሚያወጡ ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ነው ብለዋል።

አካባቢውን የመንግሥት ኃይሎች ለቀው ሲወጡ ደሞዝ እንደሚቋረጥ የሚናገሩት መምህራን በወረዳው የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራኞችም ደሞዝ እንደማይከፈላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገርም በአካባቢው መምህራን “ተለይተው” ጫና እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

“‘የዚህ ችግር [የግጭቱ] ዋነኛ ጠንሳሾቹ እናንተ ናችሁ። እየተዋጋችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ’” በሚል ጫና እንደሚደርስባቸውም የተናገሩ አንድ መምህር መታወቂያቸውን ለማሳየት ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

10 comments

ፍቅር ያሸንፋል November 27, 2024 - 8:54 am

ወዴት ያው ነው፡፡

Reply
Abbe Guta November 27, 2024 - 8:54 am

Not our business

Reply
Abdurezak Redwan November 27, 2024 - 8:56 am

ጦርነት ጎጂ ነው 😔

Reply
Nim Rad November 27, 2024 - 8:58 am

እንዴት ነው ምትሰደዱ የመምህር መታወቂያ ይዛችሁ የፋኖን kela ማለፍ አትችሉም እኮ 😂😂

Reply
Atsbha Mezgebe Amg November 27, 2024 - 9:06 am

ቻሉት አኛም ሦስት ዓመት መሉ ኔት ወርክ መብራት፣ደምወዝ፣በንክ፣መድሃኒት ፣መንገድ ሁሉ ነገር ተዘግቶብን ስትጨፍሩ ስትገድሉ ስትደፍሩ የነበራችሁ የፍኖ ደጋፊዎች ቻሉት

Reply
Abi Naldo November 27, 2024 - 9:07 am

ይኸው ነው ብልፅግናው 😏

Reply
Lidu Amhara November 27, 2024 - 9:17 am

የለገሰ ቱሉ ኢትዮጵያ ያለችው የት ይሆን🤔

Reply
Kib Keb November 27, 2024 - 9:19 am

ደሞዝ ይጠይቃል ቋሪት ጦርነት መሀል ተቀምጦ

Reply
Dagim Getnet November 27, 2024 - 9:48 am

የብልጽግና ሰወች ግን ህልማቸውን እየኖሩ ነው።

Reply
Tadele Negash November 27, 2024 - 10:00 am

ቦታው ኮንሶ ይመስላል

Reply

Leave a Comment